NEWS: Ato Lemma Megersa To Return Displaced Amharas | ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንመልሳለን – ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል ያለአግባብ የተፈናቀሉ በክልሉ ሲኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰሩ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ለማ ተፈናቃዮቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ቦታ ላይ ሰላም ቢሰፍንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉ ገልጸው፥ ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሰላሙን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሌሎች ሶስተኛ አካላት የሚሰጡ አጀንዳዎችን በመለየት ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ሊታገላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ተመሳሳይ ችግሮችን ሲፈጥሩ የነበሩ ኪራይ ሰብሳቢዎች የመልካም አስተዳደር ችግር የታየባቸው ጎሰኝነት እና አድሎ የሚያራምዱ አመራርና ሰራተኞች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት እና ህዝብ ባህል ሆኖ የቆየውን የብሄር ብረሰቦች አብሮነት ለማስቀጠልም ይሰራል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢንቨስትመንት ተቋማት አካባቢ በሰራተኛ እና አሰሪ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን በመነጋገር መፍታት ሲገባ ወደ አልተገባ ግጭት መሄድ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.