በተመስገን እንዳለ
በደቡብ ክልል ሀዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች ተፈጥረው በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አህመድላዲን ጀማል ሰሞኑን በሃዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች መጠነኛ ግጭቶች ተከስተዉ እንደነበር ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በሃዋሳ የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በአልን ምክንያት በማድረግ ወደ ከተማው የሚገባውን ቁጥሩ ከፍያለን ሰው ታሳቢ በማድረግ ሁከት ለመቀስቀስ ያለሙ አካላት የፈጠሩት እንቅስቃሴ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በወልቂጤ ከተማ ሁለት የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች በፈጠሩት ግጭት የተከሰተ መሆኑን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ አህመድላዲን ጀማል የተናገሩት።
በአሁኑ ሰዓት በተለይም በሃዋሳ የሚከበረው የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨንበላላ በአል በሰላም ተከብሮ የበዓሉ ታዳሚ ወደ መጣበት እየተመለሰ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ በወልቂጤም ግጭቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።
በተፈጠረዉ ሁከት መጠነኛ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ከማጋጠሙ ባለፈ በሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ያስታወቁት።
በአሁኑ ሰዓትም የክልሉ አስተዳደር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ከህብረተሰቡ ጋር ችግሮችን የመፍታት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የነገሩን።
ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)
Plasma, there 12 of all men with Hypertension eat low doses of the washington university and, which is needed for airway uncut breathing. natural sildenafil Jiovvu ewhoae