እርጥበት የጉንፋን ቫይረስ ስርጭትን አይቀንስም

እርጥበት የጉንፋን ቫይረስን ስርጭትን እንደማይቀንስ አንድ ጥናት አመላክቷል።

ተመራማሪዎቹ ከ2009 በኤች1 ኤን1 በተባለ የጉንፋን ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ትንፋሽ በወሰዱት ናሙና ላይ ባደረጉት ጥናት ቫይረሱ በእርጥበት የማይቀንስ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ከህሙማኑ በወሰዱት ናሙና ላይ ባደረጉት ጥናት ቫይረሱ ከእርጥበት ይልቅ በቫይረሱ የተበከሉ ሰዎች ሲስሉና ሲያስነጥሱ በሚወጡ ፈሳሾች ሊቀነስ መቻሉ ነው በጥናቱ ያረጋገጡት።

በዚሁ ጥናት በአራት የእረጥበት ደረጃዎች የቫይረሱ መጠን ለመቀነስ ተመራመሪዎች ባደረጉት ሙከራ በሁሉም ደረጃዎች የቫይረሱ መጠን መቀነስ ያለመቻሉ ነው የተገለጸው።

ጥናቱ የጉንፋን በሽታ በሰፊው በተሰራጨበት ወቅት የጤና ተቋማት ቫይረሱን ለመቀነስ የተሰራ እንደሆነ የጥናቱ ረዳት ጸሀፊና በፒትስቡርግህ ዩንቨርሲቲ የጤና ትምህረት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ሰማ ላካዳዋላ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል እርጥበት የጉንፋን ቫይረስን ይቀንሳል የሚል አስተሳሰብ የነበረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ አሁን ላይ በጉንፋን በቫይረሱ የተበከሉ ሰዎች ሲስሉና ሲያነጥሱ በሚወጡ ፈሳሾች ቫይረሱ የሚቀንስ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመላከተው።

ጉንፋን በሰፊው በሚከሰትበት ወቅትም ከእርጥበት ይልቅ ክፍሎቻችን ንጹህ አየር ማግኘት ያለባቸው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.