NEWS: ፈረንሣይ ውስጥ ከ ማሊ የመጣ ስደተኛ በሞት አፋፍ ላይ የነበረውን ህፃን በሚያስገርም መንገድ አዳነው

በፓሪስ ከሰሞኑ ከ4ኛ ፎቅ ከመፈጥፈጥ የተረፈው ሕጻን ወላጆች ማላዊውን ስደተኛ “እግዜር ይስጥልን” ብለውታል።

“ከልቡ ጀግና ነው።” ብለዋል የሕጻኑ ሴት አያት።

የማሊው ስደተኛ ጀብድ ዓለምን ካስደመመ በኋላ አዳዲስ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል።

የብዙዎች ጥያቄ እንዴት የ4 ዓመት ብላቴና በረንዳ ላይ በዚያ ሁኔታ ተንጠላጥሎ ሊገኝ ቻለ”? “ወላጆቹስ ይህ ሁሉ ሲሆን የት ነበሩ?” የሚለው ነው።

የልጁ አባት ጌም እየተጫወተ ነበር

የብላቴናው አባት በወቅቱ አንዳንድ ዕቃ ሊገዛዛ ወደ ገበያ መውጣቱ የተነገረ ሲሆን ሕጻኑን በዚያ ቸልተኝነት ጥሎ በመውጣቱ ውግዘት እየደረሰበት ነው።

ብላቴናው ሪዩኒየን ከሚባለውና አያቱና እናቱ ይኖርበት ከነበረው አካባቢ ወደ ፓሪስ የመጣው ከሦስት ሳምንት በፊት አባቱን ለማግኘት ነበር ተብሏል፤ አባቱ የሥራ ቦታው ፓሪስ በመሆኑ።

የልጁ እናትና ሌላኛው ልጃቸው በመጪው ሰኔ ወደ ፓሪስ ሊመጡ ቀጠሮ ነበራቸው።

የልጁ አባት የሚኖረው 6ኛ ፎቅ ነበር። ሕጻኑ ግን በረንዳ ላይ ተንጠላጥሎ የተገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ ነበር። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለው ጉዳይ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃንን አሁንም እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው።

ብላቴናው ከ6ኛ ፎቅ 4ኛ ፎቅ ላይ በዚያ ሁኔታ መገኘቱ ከ6ኛ ፎቅ በመውደቅ ላይ ሳለ 4ኛ ፎቅ ላይ ሲደርስ በአንዳች ተአምር ሽቦ አንጠልጥሎ አስቀርቶት ይሆናል የሚል መላምት እየተነገረ ነው።

እናትየው እንደምትለው ደግሞ የልጁ አባት ሕጻኑን ይጠብቀው የነበረው ብቻውን አልነበረም፤ ጥሎት የሄደውም ለዚሁ ነው።

“ባለቤቴ የፈጸመውን ነገር ማስተባበል አልችልም። ሰዎች ማንም ላይ የሚደርስ ነገር ነው አንቺ ላይ የደረሰው ይሉኛል። ለማንኛውም አሁን ማለት የምችለው ልጄ እድለኛ መሆኑን ነው።”

አባት ልጁን ጥሎ ገበያ ከሄደ በኋላ ወዲያውኑ ወደቤት ከመመለስ ይልቅ ጌም ለመጫወት መቆመርያ ቤት ጎራ ሳይል አልቀረም።

ጎረቤቶቹ የት ነበሩ?

4ኛ ፎቅ የነበሩ ጎረቤቶቹ ሕጻኑን ለማዳን ለምን ዘገዩ? ደግሞስ ማሊያዊው ስደተኛ ማማዱ ከምድር ተነስቶ እንደ ፌንጣ እየዘለለ 4ኛ ፎቅ እስኪመጣ ድረስ እንዴት እርዳታ ማድረግ ተሳናቸው የሚለው ሌላው መነጋገሪያ ሆኗል።

የ4ኛ ፎቅ ነዋሪዎች ለፓሪሲያን ለተሰኘ ጋዜጣ እንደተናገሩት አንደኛው ጎረቤታቸው የልጁን አንድ ክንድ ይዞ እንዳይወድቅ ለማድረግ የቻለ ቢሆንም ሳብ አድርጎ ወደ በረንዳው ለማምጣት በበረንዳዎቹ መካከል ያለው ክፍት ቦታ እንዳስቸገረው ተናግሯል።

“ነገሮችን ቀስ በቀስ ማድረጉ ይሻላል ብዬ ነው። አንጠልጥዬ ወደ በረንዳው ለማስገባት ብሞክር ልጁ ይወድቅብኛል የሚለው ፍርሃት አደረብኝ” ይላል ጎረቤቱ።

ብላቴናው በወቅቱ የስፖይደርማን ልብስ ለብሶ መታየቱ አግራሞትን ፈጥሯል። በወቅቱ አውራ ጣቱ ላይ እየደማ እንደበረና ሚስማር ክፉኛ እንደቧጨረውም ተነግሯል።

ብላቴናው አሁን የት ነው ያለው?

የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ሕጻኑን ማገገሚያ አስቀምጠው ልዩ እንክብካቤ እንዲያገኝ እያደረጉት ነው ተብሏል። አባትየው በሆነው ነገር እጅግ ሐዘን ገብቶታል፤ ለጊዜውም ከዕይታ ተሰውሯል ተብሏል።

ወላጆቹ በቸልተኝነት ላደረሱት ጉዳት የ2 ዓመት እስርና 30 ሺ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችልም ተነግሯል።

የአዳጊው ሴት አያት በበኩላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሉን ሲመለከቱ እጅግ መደንገጣቸውን ለፈረንሳይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

“የፈጣሪ ያለህ! እንዲህ ደንግጬ አላውቅም! ደግነቱ ነፍስ አዳኙ እንዴት መንጠላጠል እንዳለበት አሳምሮ ያውቃል። ብዙ ሰዎች ምድር ላይ እጃቸውን አጣምረው ቆመው ነበር። የማይታመን ጀብድ ነው የፈጸመው፤ ከልቡ ጀግና ነው!” ሲሉ አሞካሽተውታል።

ጋሳማ ማማዱ ማን ነው?

የ22 ዓመቱ ማማዱ ማላዊ ዜግነት ያለው ሲሆን አገሩን ለቅቆ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሄደው ግን በልጅነቱ ነው።

በኋላም የሰሀረ በረሃን፣ ቡርኪናፋሶን ኒጀርን እና ሊቢያን አቋርጦ በሜዲትራኒያን ሰንጥቆ ጣሊያን የገባው በ2014 ነው። የተሳካ ስደት ከማድረጉ በፊት በፖሊስ ተይዞም ያውቃል።

ማማዱ ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማርኮን እንደተናገረው ፈረንሳይ የመጣው ጣሊያን ውስጥ ማንንም ሰው ስለማያውቅና ወንድሙ ግን ፈረንሳይ ይኖር እንደነበር አብራርቷል።

አዳዲስ በሚገነቡ ሕንጻዎች አካባቢ ግብርን በመሸሽ ዝቅተኛ ሥራ በመሥራት ይተዳደር እንደነበረና ማታ ማታም አልቤርጎ እያደረ ሲኖር መቆየቱንም ለፈረንሳይ ፕሬዝዳንት አብራርቶላቸዋል።

ማማዱ እንደሚለው ጥገኝነት ለማግኘት ማመልከቻ አስገብቶ አያውቅም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

14 Comments

 1. I was wondering if you ever thought of changing the structure of your blog?

  Its very well written; I love what youve got to say.

  But maybe you could a little more in the way of content so people could connect with it better.
  Youve got an awful lot of text for only having one or
  two pictures. Maybe you could space it out better?

 2. Greetings I am so happy I found your site, I really found you by error, while I was looking on Google for something else,
  Nonetheless I am here now and would just like to say thanks a lot for a fantastic post and a all round entertaining
  blog (I also love the theme/design), I don’t have time to read through it all at the minute but
  I have bookmarked it and also added in your RSS feeds, so when I have time
  I will be back to read more, Please do keep up
  the superb jo.

 3. When I initially commented I clicked the “Notify me when new comments are added” checkbox and now each time a comment is
  added I get four e-mails with the same comment.
  Is there any way you can remove people from that service?

  Cheers! 32hvAj4 cheap flights

 4. Woah! I’m really loving the template/theme of this site. It’s simple, yet effective.

  A lot of times it’s very difficult to get that “perfect balance” between usability and visual appeal.
  I must say you have done a superb job with this. Also, the blog loads
  very quick for me on Opera. Outstanding Blog! yynxznuh cheap flights

 5. I’m really enjoying the design and layout of your website.
  It’s a very easy on the eyes which makes it much more pleasant for me to come here and
  visit more often. Did you hire out a designer
  to create your theme? Fantastic work! 32hvAj4 cheap
  flights

 6. This is very interesting, You’re a very skilled blogger.
  I’ve joined your rss feed and look forward to seeking
  more of your wonderful post. Also, I have shared your web site in my social networks!

 7. What’s Happening i am new to this, I stumbled upon this I have found It positively helpful and
  it has helped me out loads. I am hoping to contribute & help different customers
  like its helped me. Good job.

 8. Excellent web site you have here.. It’s difficult
  to find good quality writing like yours these days. I truly appreciate people like
  you! Take care!!

Comments are closed.