ሳውዲ ኢትዮጵያውን እስረኞችን ልትፈታ ነው – Saudi Arabia To Free Ethiopian Detainees

የሳዑዲ መንግሥት ኢትዮጵያውን እስረኞችን ለመፍታት ዝግጁ ነኝ አለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ኮሚዮኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ለመፍታት ዝግጁ ነኝ ብሏል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በሳዑዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ ሳውድ በተደረገላቸው ግብዣ ወደ ሳዑዲ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አቅንተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሳምንታት በፊት በጎረቤት ሃገራት ሱዳን እና ኬንያ የስራ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በመንግሥታቱ መካከል በተደረሰ መግባባት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከእስር ተለቀዋል።

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በሳዑዲ አረቢያ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ኢትዯጵያዊያን ያለ ህጋዊ ፈቃድ ይኖራሉ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.