በኬንያ የ80 ሚሊያን ዶላር የሙስና ቅሌት ተጋለጠ

የኬንያ መርማሪዎች የ80 ሚለየን የአሜሪካ ዶላር የሙስና ቅሌት አጋለጡ።

በሙስና ቅሌት መዝገቡ ላይ የተመዘገቡ የገንዘብ ዝውውሮች እንደሚያመላክቱት የመንግሥስት ሹመኞች እጃቸው አለበት ሲሉ የአቃቤ ህግ ዳሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል ።

ይህ የሙስና ቅሌት በኬንያ ከተጋለጡ ቅሌቶች የቅርቡ ሲሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥም የኬንያን ብሄራዊ ወጣቶች አገልግሎት ላይ ሲያነጣጥር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የኬንያን ብሄራዊ ወጣቶች አገልግሎት የተቋቋመው ወጣቶችን በማሰልጠን በአገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ ታስቦ ነበር።

ይሁን እንጂ ከዚህ ፕሮግራም በሥልጣንና ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል የሚሉ ጥርጣሬዎች አሉ።

ክሱ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ህጋዊ ማስመሰል እና ላልተቋቋሙ ድርጅቶች ገንዘብ መክፈል የሚሉ የሚገኙበት ሲሆን በአንዳንድ ክስተቶች ላልተሰጠ አገልግሎት ከሁለት እጥፍ በላይ ለማይታወቅ አገልግሎት አቅራቢ ክፍያ ተፈፅሟል።

በድርጅቱ የቀረቡት የገንዘብ መቀበያ ደረሰኞች ከተሰጠው አገልግሎት ጋር የሚገናኙም አይደሉም።

የህዝብ አቃቤ ህግ ዳይሬክተር የሆኑት ኖርዲን ሃጂ ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንደሚመሰረት ተናግረዋል።

ከሶስት ዓመት በፊት ተጋልጦ የነበረው የሙስና ቅሌት የምክርቤቱን ፀኃፊ ከኃላፊነት ያስነሳ ነበር።

አሁን በተጋለጠው የሙስና ቅሌት ተጭበረበረ የተባለው ገንዘብ መጠን ግን ከቀደመው በአስር እጥፍ እንደሚበልጥ ተነግሯል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.