የአሜሪካ ጠፈር ምርምር ኤጀንሲ NASA ትንሽ ሄሊኮፕተር ወደማርስ ሊልክ ነው – NASA to fly a helicopter on Mars

የአሜሪካ ብሔራዊ የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ / ናሳ / ተመራማሪዎች ስለቀይዋ ፕላኔት ያላቸውን ዕውቀት የሚያሰፋ ሰው አልባ አነስተኛ ሄሊኮፕተር ወደማርስ ለመላክ ማቀዳቸውን ስካይ ኒውስ ዘገበ፡፡

የጠፈር ምርምር ኤጀንሲው እኤአ በ2020 ከሚያከናውናቸው ጉልህ ተግባራት መካከል አንዱ በሆነው በዚህ ተልዕኮ የሰው ልጅ ከሚኖርባት ምድር ውጪ የምትገኝ ፕላኔትን እየበረረች የምታጠና ሄሊኮፕተር ሲልክ የመጀመሪያው ይሆናል፡፡

የማርስ ሄሊኮፕተር የሚል መጠሪያ ይዛ በርቀት መቆጣጠሪያ የምትንቀሳቀሰው ትንሽ ሄሊኮፕተር 1 ነጥብ 8 ኪ ግ ክብደት ሲኖራት የመቅዘፊያ ውልብልቢቷ ምድር ላይ ከሚበሩ ሄሊኮፕተሮች 10 ጊዜ በመፍጠን በደቂቃ 3 ሺ ጊዜ የመሽከርከር አቅም ይኖራታል ፤እንደተመራማሪዎቹ ፡፡

የናሳ ባለስልጣናት እንደተናገሩት ሄሊኮፕተሯ ማርስ 2020 በተባለች ተሸካሚ መንኮራኩር ወደቀይዋ ፕላኔት ከደረሰች በኋላ የማርስን ተፈጥሯዊ አሠራር በማጥናት ከባቢ አየሯ ለሰው ልጅ መኖርያነት ያለውን አመችነት ትምረምራለች መባሉን ዘገባው አብራርቷል፡፡

ምንጭ:  Amhara Mass Media Agency

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.