በርካታ ባሎችን በማግባት ክስ ተመስርቶባት በአክራሪው የሶማሊያ እስላማዊ ቡድን በሚመራ ፍርድ ቤት የቀረበች ሴት በድንጋይ ተወግራ እንደተገደለች ለታጣቂው ቡድን ቅርብ የሆነ የዜና ድረ-ገፅ ዘግበ።
ሹክሪ አብዱላሂ ዋርሳሜ የተባለችው ይህች ሴት ቀደም ካሉ ባሎቿ ጋር የፈፀመችውን ጋብቻ ሳታፈርስ አሰራ አንድ ጊዜ አግብታለች በሚል ነው የተከሰሰችው።
ተከሳሿ እስከአንገቷ ድረስ መሬት ውስጥ እንድትቀበር ከተደረገች በኋላ በታችኛው የሸበሌ ክልል ሳብላሌ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የአልሻባብ ታጣቂዎች በድንጋይ ተወግራ ነው የተገደለችው።
ዜናውን የዘገበው ድረ-ገፅ እንዳለው ተከሳሿ በሙሉ ጤንነት ላይ የነበረች ሲሆን ለቀረበባት ክስ ጥፋተኝነቷን አምናለች ብሏል።
ከአራት ዓመት በፊትም አል-ሻባብ በደቡባዊ ሶማሊያ የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባለችው የባራዌ ግዛት በተመሳሳይ በምስጢር አራት ባሎችን አግብታለች ተብላ የተከሰሰችን ሴት በድንጋይ ተወግራ እንድትገደል አድርጓል።
ምንጭ: ቢቢሲ
To slaughter a aware uninjured with held, in septic and treatment management. generic sildenafil canada Mowngi zaqbrb