Google Announces The New Android OS | ጎግል አዲሱን አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይፋ አደረገ

ጎግል አንድሮይድ P የተባለውን አዲሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለተጠቃሚዎቹ ይፋ ማድረጉ ተገለፀ።

ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ወስጥ አብዛኛዎቹ ከዚህ ቀደም የነበሩ እና ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ ተነግሯል።

ነገር ግን አዲሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለየት የሚያደርገው ስለ አጠቃላይ ጤናችን እና ስለ አእምሯችን ጤና የሚከታተል አገልግሎም አካቶ መያዙ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ላይ የተካተተው ሌላ አገልግሎት “ዳሽቦርድ” የሚባል ሲሆን፥ ይህም መተግበሪያዎችን ምን ያክል ጊዜ እና ለምን ያክል ሰዓት እንደምንጠቀም ለመለየት ይረዳናል።

አገልግሎቱ ከመጠን በላይ ለረጅም ሰዓት አብዝተን የምንጠቀመውን መተግበሪያ በመለየት የምንጠቀምበትን ጊዜ መቀነሻ መፍትሄም ይጠቁመናል ተብሏል።

ሌላው “አፕ ታይመር” የሚል አገልግሎት ሲሆን፥ ይህም አንድን መተግበሪያ በቀን ውስጥ ለመጠቀም በፈለግነው ልክ ብቻ በሰዓት ለመገደብ የሚያስችለን ነው።

አንድ ጊዜ ሰዓት ሞልተን አገልግሎቱን እየተጠቀመን ሰዓታችን ካለቀ መተግበሪያው ስራውን የሚያቆም ሲሆን፥ በቀን የተፈቀደውን ገደብ ሞልተዋል የሚል ምልእክትም አብሮት ይመጣል።

“ዊንድ ዳወን” የተባለውም በአንድሮይድ ፒ የተካተተ አገልግሎት ሲሆን፥ ይህም የእንቅልፍ ሰዓታችንን አንዴ አስተካክለን ከሞላን በኋላ ሰዓቱ ሲደርስ ቀስ እያለ እየደበዘዘ በመሄድ እንዳንጠቀም የሚከለክል ነው።

በተጨማሪም “ሳማት” የሚባለውም የዩትዩብ ተጠቃሚዎ ለረጅም ሰዓት ያለማቋረጥ ቪዲዮ እየተመለከቱ ከሆነ በመሃል እረፍት እንዲያደርጉ መልእከት የሚያስተላልፍ አገልግሎት ተካቶበታል።

አዲሱ አንድሮይድ P በተለይም የስማርት ስልክ ሱስ ተጋላጭነትን ከመቀነስ አንፃር የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.