ፆም ለአንጀት ጤና በጎ እስተዋፆ አለው – Fasting and It’s Positive Impact On Our Intestine

ተመራማሪዎቹ በአይጦች ላይ በአደረጉት ጥናት እንዳመላከቱት ለ24 ሰዓት ከምግብ በመታቀብ በአንጀት ጤና ላይ የሚከሰቱ የጤና ጉድለቶችን ለማሻሻል ይቻላል ተብሏል።

የአንጀት ግድግዳዎች በእየ 5 ቀናቱ እራሳቸውን የሚድሱ ሲሆን፥ በዚህም በአንጀት ግድግዳዎች ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች በተፈጥሮአዊ መንገድ ለማሻሻል እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጅ ሰዎች እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ይህ ዓይነቱ ዑደት እየተዳከመ እንደሜሄድ ነው በጥናቱ የተመላከተው።

በዚህ ጥናት እንደተረጋገጠው አይጦቹ ለ24 ሰዓት እንዳይመገቡ በማድረግ በአንጀት ግድገዳ ላይ የተከሰቱ የጤና ጉድለቶችን እንደገና በማገገም ሂደት ላይ ያለውን ተግባር አፋጥኖታል ተብሏል።

በኤምአይቲ የስነ ህይዎት ምርምር እና ኋይት ሄድ የምርምር ማዕከል አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ደቪድ ሳባቲ ፆም በሰውነት ውስጥ የምግብ ውህደት እንዲስተካከል በማድረግና በአንጀት ግድግዳዎች ላይ ምቹ የጤና ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች፣ የካንሰር ህሙማንና ሌሌሎች የአንጀት ችግር ላለባቸው ሰዎች የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ኤምአይቲ የስነ ህይዎት ምርምር ማዕከል እንዳረጋገጠው የሰዎች እድሜ አየገፋ ሲሄድ ለ24 ሰዓት በመፆም በአንጀታቸው ላይ ችግር የነበረባቸውና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ችግር ለመቀንስ እንደሚቻልም ነው የገለጹት።

በአዲሱ ጥናት ለ24 ሰዓት ምግብ እንዳይመገቡ የተደረጉ አይጦች አንጀት ግሉኩስን ከማድቀቅ ባለፈ ፋቲ አሲዶችንም እንዲዋሀዱ አድረጓል፣ በአንጀት ላይ የነበሩ ጉዳቶችም መሻሻሎችን አሳይተዋል ተብሏል።

በኤምአይቲ የስነ ህይወት ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰርና የካንሰር ጥናት አሳልጣኞች አባል የሆኑት ኦመር ይልማዝ እንደተናገሩት ለ24 ሰዓት ምግብ እንዳይመገቡ በተደረጉ አይጦች ላይ የተጎዱ የአንጀት ግድግዳዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ለካንሰር ህሙማንም ይሁን በእድሜ ለገፉ ሰዎች የሚኖረው ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ቀደም ሲል የካሎሪ አወሳሰድ መጠንን መቀነስ ለሰዎቹና ለሎች እንሰሳት እረጅም እድሜ ለመኖር የሚያስችል መሆኑ በሌላ ጥናት እንደተመላከተም ነው በዘገባው የተጠቆመው።
ጥናቱ ለካንሰር፣ እና ሌሎች የአንጀት ህሙማን መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ነው ተመራማሪዎች የገለጹት።

የጥናቱ ውጤት በእድሜ የገፉና በወጣት አይጦች ላይ አዎንታዊ ውጤት እንዳለውም ነው ዘገባው የሚያሰረዳው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement

3 Comments

Comments are closed.