ጣሊያን “በባለአደራ መንግሥት” ልትመራ ትችላለች

በጣሊያን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ላይ እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች አለመሳካታቸው እየተነገረ ነው። ፕሬዚዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ እንደሚሉት ከዚህ በኋላ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

አንዱ የባላደራ መንግሥት ማቋቋም ካልሆነም አዲስ ምርጫ ማካሄድ።

ባለፈው ኅዳር በጣሊያን በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ የብዙኃንን ድምጽ ማግኘት የቻለ አውራ ፓርቲ አብላጫ ወንበር ማሸነፍ አልቻለም።

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ተከታታይ ውይይቶችና ድርድሮች ሲካሄዱ ቢቆዩም አንዳቸውም ውጤት አላስገኙም።

ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገው ቁልፍ ድርድር ያለውጤት ከተበተነ በኋላ ትናንት ፕሬዚዳንት ማታሬላ እንደተናገሩት “አዲስ ምርጫ ማካሄድ ሊያስፈልግ ይችላል፤ አልያም አገሪቱ በገለልተኛ ባላደራ ቦርድ መመራት ሊኖርባት ነው” ብለዋል።

ተጽእኖ ፈጣሪ ናቸው የሚባሉት ፋይቭ ስታር እና ዘ-ሊግ በሐምሌ ወር አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ይፈልጋሉ።

አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት በሚል በተጀመረ ንግግር ቫይቭ ስታር ንቅናቄ ከቀኝ አክራሪው ፎርዛ ኢታሊያ እና ከመሐል ግራ ዘመሙ ዘ-ሊግ ፓርቲ ጋር መንግሥት ለመመሥረት ሳይፈቅድ ቀርቷል።

ፕሬዝዳንት ማታሬላ ትናንት በቴሌቪዥን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ድርድሮች ውጤት ባለማምጣታቸው የፓርቲ አመራሮች ገለልተኛ ባላደራ መንግሥት እንዲመሰረት ግፊት እንዲደያደርጉ አሳስበዋል።

“ከዚህ በላይ ልንጠብቅ አንችልም” ያሉት ማታሬላ ፓርቲዎች ፍቃዳቸውን ይስጡ፣” ሙሉ ሥልጣን ለመንግሥት ካልሰጡ ያለው አማራጭ አዲስ ምርጫ በሐምሌ ወር ማካሄድ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

ባላደራው መንግሥት የሚመሠረተው ፕሬዚዳንቱ በሚሰይሟቸው የፖሊሲ ባለሞያዎች ስብስብ ይሆናል።

ባላደራ መንግሥት እስከ ዓመቱ መጨረሻ አገሪቱን ከመራ በኋላ በ2019 አዲስ ለሚመረጠው መንግሥት ሥልጣኑን ያስረክባል።

ሆኖም እስከ ትናንት ድረስ የፋይቭ ስታር ንቅናቄም ሆነም ዘ-ሊግ ፓርቲዎች ለባላደራው መንግሥት መመሥረት ድጋፋቸውን አላሳዩም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.