የጀርመኑ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ የመጀመሪያ ሴት መሪውን መረጠ

                 

ጀርመንን በጥምር የሚመራው የጀርመኑ ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በ154 ዓመት ታሪኩ የመጀመሪያዋን ሴት መሪ መረጠ።

የቀድሞዋ የሌበር ፓርቲ ሚኒስትር አንድሪያ ኔህልስ የአምናውን ምርጫ ተከትሎ የለቀቀውን ማርቲን ሹልዝ ተክተዋል።

የ47 ዓመት ዕድሜ ባለቤቷ አንድሪያ ኔህልስ የቀድሞ ፖሊስና የፍሌንስበርግ ግዛት ከንቲባ የሆኑትን ሲሞን ላንግን አሸንፈው ነው ለዚህ ስልጣን የበቁት።

በሹመታቸውም ወቅት ባደረጉት ንግግር ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን እንዲሁም የማህበረሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ቃል ገብተዋል።

“በኢኮኖሚውና በገንዘቡ በኩል ትብብርን ለማምጣት መዋቅር ያስፈልገናል” ያሉትም የፓርቲው ስብሰባ ላይ ነው።

ጨምረውም ” በዚህ ሉላዊነት፣ ኒዎሊበራል ርዕዮተ-ዓለም በሰፈነበትና በጥነት ወደ ዲጂታል በሚቀየረው ዓለም ያጣነው ትብብርን ነው። እውነት ለመናገር በማህበራዊ ዴሞክራሲውም ይህንን አጥተናል” ብለዋል።

ል ጋር እንዴት ይሰራሉ?

የፓርቲው የግራ ክንፍ የሆነውን የወጣቱን ክንፍ በአንድ ወቅት የመሩት ኔህልስ ከንግድ ማህበራትም ጋር ቅርበት አላቸው።

ግለሰቧ በደፋር ንግግራቸው የሚታወቁ ሲሆን፤ በአነድ ወቅትም የቤት እመቤትም ሆነ የጀርመን ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እቅድ እንደሌላቸው ተናግረው ነበር።

በአውሮፓ ጥንታዊ የሆነውን የሶሻል ዴሞክራቲከ ፓርቲን 66 በመቶ ድምፅ አግኝተው ቢያሸንፉም፤ ይህ ውጤት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የፓርቲው መሪ በዝቅተኛ ውጤት ሲያሸንፍ ሁለተኛው ነው ተብሏል።

የፓርቲያቸው አባላትም ከወግ አጥባቂዋ አንጌላ ሜርኬል ጥምር ፓርቲ ጋር መቀላቀልን መደገፋቸውን አልተቀበሉትም።

ሜርኬል በቀድሞዋ ምሥራቃዊ ጀርመን ያደጉ ሲሆን ኔህልስ ደግሞ በምዕራብ ጀርመን ነው። አሁንም ነዋሪነታቸው እዚያው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሜርኬል የህክምና ዶክተር ሲሆኑ የፓርቲው መሪ አንድሪያ ኔህልስ በጀርመን ሥነ-ፅሁፍ ዲግሪ አላቸው።

ኔህልስ እንደ አንጌላ ሜርኬል ብቻቸውን የሚያሳድጓት የአንድ ልጁ እናት ሲሆኑ በእምነታቸውም ካቶሊክ ናቸው።

ምንም እንኳን ሁለቱ ሴቶች የፖለቲካ ልዩነት ቢኖራቸውም የቅርብ ግንኙነት አላቸው ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement