የተማሪዎቹን ስማርት ስልክ ለመሰናክል መለማመጃነት የሚጠቀመው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ

                 

ማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በቀላሉ እንዲረዱ ለማድረግ በርካታ የማስተማሪያ ዘዴዎች እንዳሉ ይታወቃል።

በቻይናዋ ሻንዶንግ ግዛት ዴዞሁ ከተማ የሚገኝ የአሽከርከርካሪ ማለማመጃ ትምህረት ቤት ደግሞ የተማሪዎቹን ስማርት ስልክ ለመለማመጃነት እየተጠቀመ መሆኑ ተሰምቷል።

ማሰልጠኛው ተማሪዎቹ ስማርት ሰልካቸውን በተሰመረው ቢጫ መስመር ላይ እንዲያስቀምጡ በማድረግ መኪና ማቆም፣ እንዲሁም ከተሰመረላቸው መስመር ሳይወጡ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት እንዲያሽከረክሩ ለማለማመድ እየተጠቀመ ነው ተብሏል።

ልምምድ እያደረገ ያለው ተማሪም ከመስመሩ ከወጣ ስማርት ስልኩ የሚሰበርበት ይሆናል።

ከዚህ የተነሳም በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እያንዳንዱን የመሰናክል ተግባር እና ፈተና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እያለፉ ነው ተብሏል።

የትምርት ቤቱ አለማማጆች እንደተናገሩት፥ ተማሪዎቻቸውን ለማለማመድ የተጠቀሙት ዘዴ ውጤታማ ሆኗል።

ስማርት ስልክን በመጠቀም ልምምድ ማድረግ ከተጀመረ ጊዜ እንስቶ እስካሁን የተሰበረ ስማርት ስልክ አንደሌለም አለማማጆቹ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement