ሮናልዲንሆ ጎቾ የአዲስ አበባ ቆይታውን አጠናቋል

 

                    ብራዚላዊው ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ የአዲስ አበባ ቆይታውን አጠናቋል።

በሃይኒከን አማካኝነት ለሁለት ቀናት ቆይታ አዲስ አበባ የገባው ሮናልዲንሆ፥ ቆይታውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ከተመልካቾች ጋር ከተገናኘና ከኢትዮጵያ የ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች አብሮ ከተጫወተ በኋላ ነው። 

ሙሉ ጥቁር ትጥቅ ለብሶ ወደ ሜዳ የገባው ሮናልዲንሆ በቆየባቸው ጥቂት ደቂቃዎች በአዲስ አበባ ስታድየም የተገኙ አድናቂዎቹን ያስገረሙ ክህሎቶቹን አሳይቷል። 

የአለም ዋንጫ አሸናፊው ሮናልዲንሆ ጎቾ የሁለት ቀናት ቆይታውን አጠናቆ ነገ እንደሚመለስ ታውቋል።

ጎቾ ትናንት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በመያዝ ትናንት በሂልተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፤ ማምሻውን ከተመልካቾች ጋር በተዘጋጀ መድረክ ተዋውቋል። 

ከጋዜጠኞች ለተነሱለት በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቅሶ፥ ስለ ሀገሪቱ የበለጠ ማወቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል። 

ከሰዓት በኋላ በነበረው ቆይታም የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ብራዚላዊውን ኮከብ በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል። 

በቆይታው የኢትዮጵያን ስም በታላላቅ አትሌቶቿ እንደሚያውቅ ገልጿል፤ በወቅቱም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባህላዊው የጃኖ ልብስ ስጦታ ተበርክቶለታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement