የእናትና አባቱ ህይወት ካለፈ ከ4 ዓመታት በኋላ የተወለደው ጨቅላ

               

ቻይና ውስጥ በመኪና አደጋ እናትና አባቱን ያጣው ጨቅላ ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ተወልዷል።

ጨቅላው ወደዚህች ምድር ለመምጣት የበቃው በውሰት ማህጸን አማካኝነት ነው ተብሏል።

ሁለቱ ጥንዶች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 ነበር ይህን ዓለም የተሰናበቱት።

ታዲያ ከህልፈታቸው ቀደም ብሎ በርካታ የመውለድ ሙከራዎችን እያደረጉ እንደነበር ተገልጿል።

እንዲሁም በዘመናዊ መልኩ ለሚደረጉ ህክምናዎች የዘርፍሬና እንቁላሎችን በመለገስ ልጅ በመጠባበቅ ላይ ነበሩ ተብሏል።

ከአደጋው በኋላ የሟቾቹ አራት ወላጆች በህግ ተከራክረው ከማህጸን ውጪ ያስቀመጡትን ሽል እንዲጠቀሙበት ተፈቅዶላቸዋል።

አደጋው በተፈጠረበት ወቅት ሽሉ በህክምና ማዕከሉ ውስጥ በኔጌቲቭ 196 ዲግሪ በሆነ በፈሳሽ ናይትሮጅን ማቆያ ውስጥ ነበረ ተብሏል።

የውሰት ማህጸን ባለቤተዋ የላዖስ ዜግነት ያላት ሲሆን በጎብኚ ቪሳ ወደ ቻይና የገባች እንደሆነች ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት የልጁ ዜግነት ሌላ ችግር ሆኗል ይላሉ።

የልጁ አያቶች ታዲያ ማቾቹ ቻይናውያን ስለመሆናቸው የደምና የዘረመል ናሙና ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement