በሰውነት ውስጥ ያለን የአልኮል መጠን የምታሳወቅና በእጅ ላይ የምትጠለቅ አነስተኛ መሳሪያ ተዘጋጀች

                       

በሰውነታችን በተለይ በደም ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን በተከታታይነትና ለረጅም ጊዜ መቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ እንደተዘጋጀ ተነገረ።

እጅግ አነስተኛ ስትሆን ዘመናዊ የእጅ ሰዓት አይነት መጠን ያላት ስትሆን በእጅ የምትጠለቅ ገመድ አልባ መሳሪያ ናት ተብሏል።

መሳሪያዋ በአልኮል ሱስ፣ በአደገኛ ዕፅ እና በሌሎች ሱሶች የተጠቁትን ሰዎች ጤንነት ክትትልን ውጤታማ ማድረግ እንደምታስችል ተነግሯል።

ከዚህ በፊት የሰዎችን የሱስ ተጋላጪነት ለመለካትና ለማወቅ ታማሚዎች ከሚሰጡት አስተያየት በመነሳት የህክምና አገልግሎት ሲሰጥበት የቆየውን ልማድ መቀየር የምታስችል መሳሪያ መሆኗም ተነግሯል። 

ተከታታይነት ባለው ሂደት ህክምና የሚሰጥባት መሳሪያዋ ያልምንም ቀዶ ህክምና በጤና ተቋማት ህክምና ማድረግ የሚያስችልን እድል ፈጥራለች ነው የተባለው።

መሳሪያዋ አነስተኛ ሀይልን የምትጠቀም በመሆኑ በባትሪዋ በኩል ሰዎች በመርዛማ ነገሮች እንዳይጠቁ ያስችላልም ተብሏል።

በዚህም በመሳሪያዋ የተሰበሰበ መረጃ በሶስት ሰከንዶች ለመለከታ እንደሚረዳ ተገልጿል።
እንዲሁም መሳሪያዋ ዘመናዊ የእጅ ሰዓት ስራውን በሚያከናውንበት መንገድ የሚንቀሳቀስ እንደሆነ ተነግሯል።

የመሳሪያዋን ውጤታማነት ህይወት ባለቸው እንስሳቶች እንደሚያረጋግጡ ነው ተመራማሪዎቼ ያስታወቁት።

በቀጣይ ጊዜያት ሰዎችን ከሱሰኝነት ለማላቀቅ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement