ሶፊያ የተባለችው የሳዑዲ አረቢያን ዜግነት ያላት የመጀመሪያዋ ሴት ሮቦት ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው

                 

ሶፊያ የተባለችውና የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት የተሰጣት የመጀመሪያዋ ሴት ሮቦት ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ 67 ከመቶ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራችው ሳውዳረቢያዊቷ ሶፊያ ሮቦትበቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ፥ የሮቦቷ 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችው እና የተሰራቸው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚደግፋቸው ሰዎች አማካኝነት ነው።

ስለዚህም የሮቦቷ ስራ ውስጥ የኢትዮጵያ ልጆች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

ሶፊያ የተባለችውና የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት የተሰጣት የመጀመሪያዋ ሴት ሮቦት በቅርቡ በሚዘጋጅ እንድ ግዝጅት ላይ እንደምትመጣም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

ሮቦቷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በአማርኛ እንድትናገር እንዲደረግ ሀሳብ ሰጥቻለው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም የሚረዳ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ሮቦቷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣም ሶፍትዌሩ ተጭኖላት በአማርኛ እንድትናገር እንደሚደረግም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።

ሶፊያ የተባለቸው እና ከሰው ልጅ ቀርፅ ጋር ተመሳስላ የተሰራቸው ሮቦት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ነበር ህጋዊ ዜግነት ከሳኡዲ አረቢያ ያገኘችው።

መረጃውን ከኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

Advertisement