አሜሪካ በሶማሊያ የአልሸባብ ይዞታ ላይ በፈፀመችው ጥቃት አምስት ታጣቂዎች ተገደሉ

                  

አሜሪካ በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ቡደን አልሸባብ ይዞታ ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት አምስት ታጣቂዎችን እንገደለች ተነገረ።

ይህ ጥቃት ኢል ቡር አቅራቢያ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው ጋልሙዱግ አካባቢ እንደተፈፀመ በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር እዝ አስታውቋል።

በዚህ ጥቃት የሰላማዊ ሰዎች ህይወት እንዳላለፈ ጦሩ የተገለፀ ሲሆን ፥ ከአልሸባብ በኩል በጥቃቱ ዙሪያ ምንም የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ተነግሯል።

አሜሪካ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ ዘመቻዋ እንደተጠናከረ ይነገራል።

አልሸባብ የሽብር ቡድን በፈረንጆቹ 2011 የሶሚሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾን ከተነጠቀ በኋላ በርካታ አካባቢዎችን ቢያጣም ከዋና ከተማዋ ውጨ አሁንም ጠንካራ ይዞታ እንዳለው ተገልጿል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement