ቀድሞ ለአቅመ ሄዋን መድረስ ከአልተፈለገ የሰውነት ክብደት ጋር ቁርኝት አለው – ጥናት

              

ቀድመው ለአቅመ ሄዋን የሚደረሱ ሴቶች በቀሪ ህይወታቸው ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት እንደሚጋለጡ ተመራማሪዎቹ ገለጹ።

በጥናቱ ለአቅመ ሄዋን ቀድመው የደረሱ ሴቶች በቀሪ ህዎታቸው ላልተፈለገ የሰውነት ክብደ በመጋለጣቸው በሰውነታቸው ውስጥ የስብ መጠን ክምችት ታይቶባቸዋል ነው የተባለው።

የብሪታኒያ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ተመራማሪዎች በመቶ ሺህ በሚቆጠሩ ሴቶች ላይ ጥናቱን እንዳካሄዱ ተገለጿል።

የሴቶች ለአቅመ ሄዋን ቀድሞና ዘግይቶ መድረስ በቀሪ ህይወታቸው ካልተፈለገ የሰውነት ክብደት መጨመር ጋር ቁርኝት እንዳለው አረጋግጠዋል።

እንደ አጥኚዎቹ ሀሳብ ከዚህ ቀድሞ በጉዳዩ ላይ ጥናት ተደርጎ የነበረ ሲሆን ዘር፣ የኢኮኖሚ መሰረት፣ የትምህርት ደረጃ፣ አመጋገብና የመሳሰሉት ጉዳዮች በጥልቀት ያልተዳሰሱ እንደነበር ታውቋል። 

ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትና የሴቶች ለአቅመ ሄዋን መድረስ ግንኙነት እንዳላቸው ቀድሞ የሚታወቅ ቢሆንም መዘግየቱ ይሁን መቅደሙ ተጽህኖ እንዳለው ግልጽ እንዳልነበር ዘገባው አስረደቷል።

ጥናቱ ከአካላውና ስሜታዊ ጉዳዮች ጋር ቁርኝት እንዳለውና ቀድመው ለአቅመ ሄዋን የሚደርሱ ሴቶች ለተለያዩ መሀበረሰባዊ ጫናዎች እንደሚጋለጡ ያስረዳ እንደነበር በዘገባው ተገለጿል።

በአዲሱ ጥናት ከለይ የተጥቀሱት ተለዋዋጮች በሰፊው በመዳሰስ በጥናቱ ቀድመው ለአቅመ ሄዋን የሚደርሱ ሴቶች በቀሪ ህዎታቸው ለአልተፈለገ የሰውነት ክብደት እንደሚጋለጡ በምርምሩ የተሳተፉት ዲፐንደር ጊል ተናግረዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement