የቀድሞው የፈረንሳይ መሪ ኒኮላስ ሳርኮዚ በቁጥጥር ስር ዋሉ

                              

የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዘደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ከሟቹ የሊቢያ መሪ ሙዐሙር ጋዳፊ ገንዘብ ተቀብለዋል በሚልከ ክስ በፈረንሳይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘገበ።

የሃገሪቱ ፖሊስ በ2007 በፈረንሳይ ምርጫ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኒኮላስ ሳርኮዚ ከጋዳፊ ገንዘብ ተቀብለዋል ሲል ያሰራቸው።

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ክስ ስማቸው የተጠቀሰው ሳርኮዚ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ሲሉ መካዳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

የፈረንሳይ ፖሊስ በዚህ ጉዳይ ምርመራውን የጀመረው በአውሮፓውያኑ 2013 ሲሆን የክሱ ዋነኛ ጭብጥ የሳርኮዚ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ከጋዳፊ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ተደጉሟል የሚል ነበር።

ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የሳርኮዚ ቀኝ እጅ የሆኑት ብሪስ ኦርተፈም በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሎችም የንግድ ሰዎችና ባለስልጣናት በተመሳሳይ ክስ እንደሚፈለጉ ለማወቅ ተችሏል።

‘ለ ሞንድ’ የተሰኘው የፈረንሳይ ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞ የሊቢያ የፋይናንስ ሚኒስተር የሆኑት ባሽር ሳሌህ ሳርኮዚ ከጋዳፊ እንተቀበሉ አረጋግጠዋል።

ሳርኮዚ ለ48 ሰዓታት ያህል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ሊለቀቁ እንደሚችሉና ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል የህግ ባለሙያዎች እያስረዱ ይገኛሉ።

ከጋዳፊ ጋር ከተያያዘው ክስ ባለፈ የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዘደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ለምርጫ ቅስቀሳ በሚል በህገ-ወጥ መልኩ ግንዘብ አሰባስበዋል በሚል በፖሊስ ይፈለጋሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement