መብረቅ የሩዋንዳ ምዕመናንን ሕይወት ቀጠፈ – Rwanda Seventh-Day Adventist Churchgoers Killed by Llightning

                                 

ዕለተ ቅዳሜ በሩዋንዳ ደቡባዊ ግዛት የጣለው መብረቅ 16 የአምልኮ ሥርዓት ላይ የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስትያን ምዕመናንን ነብስ አጥፍቷል።

አብዛኛዎቹ ተጎጂዎቹ ወዲያውኑ ሕይወታቸው እንዳለፈ አደጋው የደረሰበት የሩዋንዳዋ ኒያሩጉሩ ከተማ ከንቲባ ሃቢቲጌኮ ፍራንስዋ ተናግረዋል።

ወደ ሆስፒታል ካቀኑት 140 ምዕመናን መካከል ሁለቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ የተቀሩቱ ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነም ታውቋል።

ይህ አደጋ ከመድረሱ አንድ ቀን በፊት ዕለተ አርብ በዚያው አካባቢ የደረሰ መብረቅ አስራስምንት ተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሶ አንድ ተማሪ መግደሉም ተነግሮ ነበር።

በአካባቢው እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዝናብ ለአደጋው መንስዔ መሆኑንም የአካባቢው ባለሥልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ መንግስት የህንፃ ግንባት ህግ ጥሰዋል እንዲሁም የድምፅ ብክለት እያስከተሉ ነው ያላቸውን 700 ቤተ እምነቶች መዝጋቱ አይዘነጋም።

የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃንም ከተዘጉት ቤተ-አምልኮዎች መካከል አብዛኛዎቹ የመብረቅ መከላከያ መሣሪያ እንደሌላቸው በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement