ፍቅር ማለት….

                               

ፍቅር በከንፈር መሳም ከሆነ የይሁዳ ፍቅረኛ አልፈልግም። ሲወደኝ በከንፈሩ እየሳመ ሲጠላኝ በእጁ አሳልፎ ለበደል ይሰጠኛል ። ፍቅር ገንዘብ ከሆነ ነጋዴ ፍቅረኛ አልፈልግም። በከፈለው ልክ ሲከፍለው ይሸጠኛል። ተከፍሎኝ የምወደድ ወርቅ አይደለሁም። ስጠላም የሚሸጡኝ ሰልቫጅ አይደለሁም። ፍቅር እውር ከሆነም በስሜት ጨለማ መፈቀር አልፈልግም። ዛሬ በስሜቱ እያወራ የወደደኝ ብርሀን ሲበራለት ይጠላኛል ፍቅር ውበት ነው። ውበት ደግሞ የልዩነት ውህደት ነው። ጠንካራ ፍቅር በልዩነት የሚሳል ስዕል ነው ድክመት የጥንካሬ ሸራ ሲሆን በፍቅር ይሸፈናል። አውቆ የተሸፈነ ሲገለጥ

አያስጠላም። ተደብቆ የተሸፈነ ሲገለጥ ያስደነግጣል። መወደድ የምፈልገው በጥንካሬዬ አይደለም። በድክመቴ የሚወደኝ እሱ የፍቅር ውበት ነው። በጥንካሬ ብቻ የሚወድ የነገ ጠላት ነው። ዛሬ በጥንካሬ
የወደደህ ነገ ስትደክም ይነሳብሀል። ድክመትህን ሸፍነህ ለፍቅር ከቀረብክ ያለምሽግ የሚታኮስ ወታደር ነህ። ድክመትህ ሲጋለጥ ተመተህ ትወድቃለህ። ለመፈቀር ብለህ አታስመስል። አስመስለህ በቀረብከው ተወደህ ከምትጠላ ራስህን ሆነህ ብትኖር የሆንከውን የምትወድ/የሚወድ አታጣም። በዚህ ጊዜ ፍቅር ውበት ሆኖ ያስደስትሀል።

ምንጭ፦ ከፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ

Advertisement