የአዲሱ ሳምሰንግ ጋላክሲ S9 በካሜራ ብቃት ላይ አተኩሯል – The New Samsung Galaxy S9 Model Focused on Camera Capabilities

                                       

የጋላክሲ S9 እንዲሁም S9+ ካሜራዎች አቅም ከፍተኛ እንዲሆን ማድረግ የአዳዲሶቹ የሳምሰንግ ምርቶች መገለጫዎች ናቸው።

የሁነቶችን እንቅስቃሴ መቅረፅ የሚያስችል ካሜራ አሰራር እንዲሁም አነስተኛ ብርሃንን ማሻሻል የሚችሉ ሌንሶች የእነዚህ ስልኮች መለያ ነው።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 የሳምሰንግ ሽያጭ ጨምሮ የነበረ ቢሆንም እንደ ሌሎቹ ተቀናቃኝ የቻይና ኩባንያዎች ግን ሽያጩ በጣም አልጨመረም።

ኤክስፐርቶች እንደሚሉት አሁን ምርቶቹ ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎችም ቀላል እንጂ ጉልህ የሚባሉ አደሉም።

ይሁንና የs9 ቅርፅ ከ s8 ጋር እጅግ የሚመሳሰል መሆኑ ለአዲሶቹ ስልኮች ሽያጭ ችግር ሊሆን እንደሚችልም ይናገራሉ። S9+ ብቻ ከ S8+ በደንብ ይለያል።

ሁለቱ የካሜራ ሌንሶች የተያዩ እይታዎችን ይሰጣሉ፤ ትኩረት ከሚደረግበት ነገር ውጭ ያለን ነገር ገፅታንም እንደተፈለገው ለማድረግ ያስችላሉ።

“የተደረጉት ማሻሻያዎች ሰዎች ስልካቸውን ለመለወጥና አዳዲሶቹን ለመግዛት የሚገፋፉ አይመስለኝም” ይላል አይዲሲ በተሰኘው ኩባንያ የገበያ ጥናት ኤክስፐርት የሆነው ፍራንሲስኮ ጀሮሚዮ።

የስልኮቹ ካሜራ መሻሻል በርካቶች አዲሶቹን ስልኮች እንዲገዙ ሊያደርጉ ቢችሉም ይጠብቅ የነበረው ማሻሻያ ከዚህ የበለጠ እንደነበር ኤክስፐርቱ ያስረዳል።

ከጠበቃቸው ማሻሻያዎች መካከል ለምሳሌ የኢንተርኔት ቀጥታ ትርጉም አንዱ ነበር። በተቃራኒው አዲሱ የቺፕ ቴክኖሎጂያቸው ምስጋና ይግባውና ያለ ኢንተርኔት ቃላት የሚተረጉሙትን የህዋዌ አዳዲስ ስልኮች ያደንቃል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement