አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የ533 ሚሊየን ዶላር የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች – US Donates 533 Million USD to African Countries, Including Ethiopia

                             

አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የ533 ሚሊየን ዶላር የሰብአዊ ድጋፍ እንደምትለግስ ይፋ አድርጋለች።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬእክ ቲለርሰን ይፋ ያደረጉት የሰብአዊ ድጋፉ ለኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ናይጄሪያን ጨምሮ በቻድ ወንዝ ክለል አካባቢ በእርስ በእርስ ግጭት እና በድርቅ አማካኝነት ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ሰዎች የሚውል ነው።

አሁን የተደረገው እርዳታ የሰዎችን ሀይወት መታደግ የሚችል ቢሆንም፤ የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ግን አይችለም፤ ምክንያቱ ደግሞ አብዛኛው ችግሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው ነው ብሏል የአሜሪካ መንግሰት ባወጣው መግለጫ።

የአሜሪካ መንግስት እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ በጋራ ባደረጉት አዲሱ ድጋፍም፥ የአሜሪካ መንግስት ለረሃብ እና ለሰብአዊ ቀውስ ለተጋለጡ ሰዎች በአፋጣኝ ምግብ እና ሌሎች ገንቢ ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል መግለጫው።

በተጨማሪም የገንዘብ ድጋፉ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ስርጭት ለመቆጣጠር እንዲቻል ለንጹህ የመጠጥ ውሃ እና ለንጽህና አጠባበቅ መርሃ ግብር የሚውል ሲሆን፥ በግጭት አማካኝነት የተለያዩ ቤተሰቦችን መልሶ ለማገናኘት የሚያግዝ ነው ተብሏል።

እንዲሁም የሰዎችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎችን ለማቅረብ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች በአፋጣኝ መጠለያ እንዲያገኙ እና ለንፅህና አጠቃቀም ስራዎች እንደመኒውል ታውቋል።

ከአዲሱ የገንዘብ ድጋፍ ውስጥም 110 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ሰዎች የሚውል ነው ተብሏል።

184 ሚሊየን ዶላሩ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ፣ 110 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ እንዲሁም ከ128 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ደግሞ በናይጄሪያና በቻድ ወንዝ ክልል ለሚገኙ ህዝቦች የሚውል መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ድርቅ በሀገሪቱ የምግጥ እርት እንዲያጋጥም አድርጓል ያለው የአሜሪካ መንግስት፥ በቻድ ወንዝ ክልል እና በደቡብ ሱዳን ደግሞ ለዓመታት የዘለቀው የእርስ በእርስ ግጭት አካባቢው ለከፋ የምግብ እጥረት እንዲጋለጥ አድርጓል።

በሶማሊያ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶች ሀገሪቱ ለከፋ የሰብአዊ መብት ቀውስ እና ለረሃብ እንድትጋለጥ አድርጓታል ብሏል የአሜሪካ መንግስት።

አሜሪካ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ብቻ ወደ 3 ቢሊየን የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች::

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement