በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሰጠመው አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከ76 ዓመታት በኋላ ተገኝቷል – 76 years later, The World War II Carrier Ship Discovered

                                  

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሰጠመው የ ዩ ኤሱ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በአውስትራሊያ ባሕራ ዳርቻ ተግኝቷል።

ዩ ኤስ ኤስ ሌክሲንግተን የተሰኘው ይህ መርከብ በምሥራቅ አውስትራሊያ 800 የባሕር ዳርቻ ርቀትና በ3ኪ.ሜ ጥልቀት ነው የተገኘው።

መርከቡ እ.ኤ.አ በ1942 ግንቦት 4 እስከ 8 ባሉት ቀናት መካከል በአውስትራሊያ ባሕር ዳርቻ የጠፋ ሲሆን በወቅቱም ከ200 በላይ መርከበኞች መሞታቸው ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል መርከብ የተገኘው የማይክሮስፍት መሥራች መካከል አንዱ በሆኑት ፖል አለን በመሩት ቡድን ነው።

የተነሱት ምስሎች ስብርባሪው በደንብ የተጠበቀ መሆኑን ያሳያሉ።

የሌክሲንግተን ግኝትና ከያዛቸው ሠላሳ አውሮፕላኖች መካከል አስራ አንዱ መገኘታቸውን ቩልካን የተሰኘው የአለን ድርጅት ባለፈው እሁድ ነበር ይፋ ያደረገው።

የፓሲፊክ ባሕር ኃላፊ የሆኑት አድሚራል ሐሪ ሐሪስም ስለግኝቱ አመሥግነዋል።

”የዩኤስ ሌክሲንግተን ሲሰጥም ከተረፉት መካካል አባቴ ይገኝበታል፤ ስለዚህ ፖል አልንንና የመርከቡን ፍለጋ ያካሄደውን ቡድን ላመሠግን እወዳለሁ” ብለዋል።

                                   

አጭር የምስል መግለጫመርከቡ ሲሰጥም 35 አውሮፕላኖችን ይዞ ነበር

በፓሲፊክ ባሕር ላይ ጃፓን እንዳትጠጋ በመገደብ ትልቅ ሚና የተጫወተው ይህ በአውስትራሊያ ባሕር ዳርቻ ላይ የተደረገው ጦርነት ነበር።

በተደጋጋሚ የጃፓን ቶረፒዶዎችና ቦምቦች ሲያገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች ሌከሲንግተን ወደባህሩ የታችኛው ክፍል እንዲሰጥም አደረጉት።

የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል መርከቡ ከተጠቃ በኋላ 216 መርከበኞች መሞታቸውን ከ2000 መርከበኞች በላይ ደግሞ ሕይወታቸው መትረፉን ገልጿል።

”ሌክሲንግተንን ፍለጋ ነበር አጀማመራችን ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከጠፉት መርከቦች መካከል ዋናዋ ነበረች” በማለት የቨልካን ቃል አቀባይ የሆኑት ሮበርት ክራፍት ተናግረዋል።

ፔትሬልን በመጠቀም ያነሷቸውም ምስሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የሌክሲንግተን ሰሌዳ ቁጥርና የጦር መሣሪያዎች አሉ። በመርከቡ ላይ የነበሩትም አንዳንድ አውሮፕላኖች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ይታያል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል እንደ ጦርነት መቃብር ስለሚቆጥረው መርከቡን ከባሕር የማውጣት ሃሳብ የለም።

አቶ ሮበርት እንደተናገሩት መርከቡን ማግኘት የቻሉት ከስድስት ወራት ዕቅድ በኋላ ነው።

                                   

አጭር የምስል መግለጫየሌክሲንገትን አንደኛው የአውሮፕላን ጥቃት መከላከያ የጦር መሣሪያ

ባለፈው ዓመት ቨልካን የተሰኘው ድርጅት በ1945 የሰጠመውን የዩናይትድስ ስቴትስ ኢንዲያናፖሊስን አግኝቶ ነበር።

በወቅጠዑ ከሰጠሙትም መካከል ሙሳሂ የተሰኘውን የጃፓን፣ አርቲሊዬሬ የተሰኘውን የጣሊያን የባሕር ኃይል መርከብና ሌሎችንም ያገኘ ድርጅት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement