የጣልያን ምርጫ ቅድመ ትንበያዎች አንድም ፓርቲ አብላጫ ድምፅ አለማግኘቱን አሳዩ – The Preliminary Estimates of The Italian Election Have Shown That no Party Has a Majority Vote

የጣልያን ምርጫ ትንበያዎች የፓርላማውን መቀመጫ በአብላጫ ድምፅ ያሸነፈ ፓርቲ እንደሌለ አስታወቁ።

በጣልያን፣ መራጮች ድምፃቸውን ለቀኝ ክንፍ እና ለፖፑሊስት ፓርቲዎች በመስጠታቸው የፓርላማውን አብላጫ ድምፅ ያገኘ ፓርቲ አለመኖሩን እስካሁን ከተቆጠሩ ድምፆች ተነስተው ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልሲዮ በርሎስኮኒ የታችኛውን ፓርላማ አብዛኛው መቀመጫን አሸንፈዋል።

ከ316 መቀመጨጫዎች መካከል ከ248 እስከ 268 ማግኘታቸው እየተነገረ ነው።

                                  

በጣሊያን መንግሥት ለመመሥረት ለሳምንታት ድርድር እና ጥምረት መፍጠር ሊያስፈልግ ይችላል።

ምንም እንኳ አስተማማኝ ባይሆንም ወሳኝ የሆነ ድምፅ ለማግኘት ሌላ ምርጫ ሊካሄድም ይችላል።

‘ኢል ፋቶ ኮቲድያኖ’ የተሰኘው የጣልያን ጋዜጣ በፊት ገጹ ላይ በአብይ ርዕስነት ሁሉም ነገር ይለወጣል ሲል አስነብቧል።

አሁን ባሉት መረጃዎች ምንም እንኳ አንድም ፓርቲ ብቻውን መንግሥት መመሥረት የሚችልበትን ድምፅ ባያገኝም ፖፑሊስት የሆኑት ፓርቲዎች ያጘኙት ድምፅ ግን ከብሬግዚት እና ዶናልድ ትራምፕ ጋር ሊነፃጸር ይችላል።

የምርጫ ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በቀዳሚነት የአውሮፓ ሕብረት ላይ ጥርጣሬ ያላቸው፣ ‘ፋይቭ ስታር ሙቭመንት’ በሁለተኛ ደረጃ እና የ’ሴንተር ራይት’ ጥምረቶች ቀጥሎ ድምፅ አግኝተዋል።

በ2009 በኮመዲያን ቤፔ ግሪሎ የተመሠረተው እና በጣልያን ፖለቲካ ውስጥ ያለውን በትውውቅ እና በወዳጅነት መሥራት የሚኮንነው፣ ‘ፋይቭ ስታር’ ከ216 እስከ 236 ድምፅ በማግኘት የታችኛውን ፓርላማ መቀጫ የሚያሸንፍ ብቸኛ ፓርቲ ይሆናል።

በሥራ አጥነት እና በስደተኝነት ላይ ሕዝባዊ ቁጣ ተቀስቅሶ ገዢውን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ፈትኖታል። የ’ሴንተር ሌፍት’ ጥምረቱ በርቀት ቢሆን ሶስተኛ ይሆናል ተብሎ ግምት ተሰጥቶታል።

የግብርና ሚኒስትሩ ማውሪትዝዮ ማርቲና “ይህ ለኛ ግልፅ ሽንፈት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

የመጨረሻ ውጤቱ በቅርብ ሰዓት ይታወቃል ተብሎ አይጠበቅም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement