በደቡብ አፍሪካ ተከስቶ ለነበረው አደገኛ የምግብ መመረዝ ምክንያቱ ታወቀ – The Cause of Dangerous Food Poisoning in South Africa Was Discovered

                                    

በደቡብ አፍሪካ ባለፈው አመት 180 ሰዎችን የገደለውን አደገኛ የምግብ መመረዝ መከሰቻ አግኝቸዋለሁ ስትል ተናገረች።

መነሻውም በኢንተርፕራይዝ ፉድስ በሚንቀሳቀስ ፋብሪካ ውስጥ ነው።

በአሁኑ ሰአት ለአንድ ሺህ ሰዎች በበሽታው መያዝ አስተዋፅኦ አድርገው ይሆናል በሚል በርካታ ተቋማት ላይ ፍተሻ እየተደረገ ነው።

የጤና ሚኒስትሩ በሱቆች ውስጥ በንክኪ ምክንያት በፋብሪካ በተቀነባባሩ የስጋ ምርቶች አማካኝነት የተነሳውን በሽታ ሊዛመት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

“በፋብሪካ የተቀነባበረ እና ለመመገብ የተዘጋጀን የስጋ ምርትን ባጠቃላይ አስወግዱ “ሲሉም እሁድ እለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል የጤና ሚኒስትሩ ሞትሶሌዲ።

በአንዳንድ ሰዎች ላይ በሽታው ከፍተኛ ትኩሳት ፣ ማስመለስ እና ተቅማጥ የሚያስከትል ሲሆን በእድሜ የገፉ፣ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ፣ ሕፃናት እንዲሁም በእናቶች ያለ ፅንስም ሆኑ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።

ከፋብሪካው ከተወሰዱ ከ16 በላይ ናሞናዎች ሊስቴሪያ ሞኖሳይቶጂነስስ የተባለው ባክቴሪያ ዝርያ ተገኝቷል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ እንዳሉት በነዚህ ፋብሪካዎች የተመረተ ለመመገብ ዝግጁ የሆነ ቋሊማ ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብ ታዝዟል።

በእነዚህ ፋብሪካዎች የተመረቱ ምግቦችንም ገዝተው በቤታቸው ያስቀመጡ ግለሰቦች በፍጥነት በኬሚካል እንዲያፀዷቸውም ተጠይቋል።

ሊስቴሪያ ባክቴሪያ በምግብ ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተሰራጭቶ ስለማይገኝ ለመመርመር እጅግ አዳጋች ነው። በፋብሪካ ውስጥም በተለያዩ ክፍተቶች ውስጥ ተደብቆ ሊገኝ ይችላል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement