አትሌት ጫላ አዱኛ በልምምድ ላይ እያለ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቱ አለፈ – Athlete Chala Adugna Bekele Died During Training

                                 

የማራቶን ሯጩ አትሌት ጫላ አዱኛ በልምምድ ላይ እያለ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው፥ አትሌት ጫላ አዱኛ በትናንትናው እለት ልምምድ በማድረግ ላይ እያለ በድንገት በያዘው የኤሌክትሪክ ገመድ ምክንያት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

አትሌት ጫላ አዱኛ የኦሮሚያ ማረሚያ ክለብን በቅርቡ የተቀላቀለ ሲሆን፥ በተለያዩ በግል የተካሄዱ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

በቅርቡም ሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ መግባት የቻለ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

እንዲሁም በጀርመን ሃኖቨር በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይም 2 ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ42 በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችሎ ነበር።

አትሌት ጫላ አዱኛ ኢትዮጵያን በማራቶን ውድድርን ለመወከል ተስፋ ተጥሎበት ነበር ያለው ፌዴረሽኑ፥ በአትሌቱ ድንገተኛ ሞት ተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፤ ለቤተሰቦቹም መፅናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement