የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ተቋቋመ – The State of Emergency Board Has Established

                               

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድን ዛሬ አቋቁማል።

መርማሪ ቦርዱ ሰባት አባላት የሚኖሩት ሲሆን፥ ዛሬ የስድስቱ አባላት ዝርዝር ቀርቦ በምክር ቤቱ ፀድቋል።

በዚህም መሰረት፦

አቶ ታደሰ ወርዶፋ
ወይዘሮ ገነት ታደሰ
ወይዘሮ ኑሪያ አብዱርሃማን 
ወይዘሮ ኪሚያ ጁነዲን 
አቶ ካሚል አህመድ እና 
አቶ ክፍለፅዮን ማሞ የመርማሪ ቦርዱ አባል ተደርገው ተመርጠዋል።

መርማሪ ቦርዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩትን ግለሰቦች ስም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ያለው ሲሆን፥ የታሰሩበትን ምክንያትንም ይገልፃል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢሰብዓዊ እንዳይሆኑ የመቆጣጠር እና የመከታተል ተግባርንም ያከናውናል።

ማናቸውም የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢሰብዓዊ መሆኑን ሲያምንበት መርማሪ ቦርዱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት እርምጃውን እንዲያስተካክል ሀሳብ ይሰጣል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈፅሙትንም ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ መርማሪ ቦርዱ ለሚመለከተው ያሳውቃል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀረብም ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ያቀርባል።

በበላይ ተስፋዬ እና ዳዊት መስፍን

 

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement