ከመስከረም ወር ጀምሮ ህግ የጣሱ አሽክርካሪዎች 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተቀጥተዋል

                                

በታሪክ አዱኛ

በተሻሻለው የአሽከርካሪዎች የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት ከመስከረም 2010 ዓ.ም ጀምሮ ህግ የጣሱ አሽክርካሪዎች 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተቀጥተዋል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው፥ ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ መስመር ባለመሸፈን እና አቆራርጦ በመጫን ህገ ወጥ ተግባር የፈጸሙ አሽከርካሪዎች ናቸው በገንዘብ የተቀጡት።

በመዲናዋ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ህግን ተከትለው እንዲያገለግሉ ግንዛቤ የማሳደግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፤ የባለስልጣኑ የትራንስፖርት ስምሪት ዳይሬክተር አቶ ጆኒ ተረፈ።

ይሁን እንጂ ከማስተማር በዘለለ በህገ ወጦች ላይ በተወሰደ የገንዘብ ቅጣት 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።

አቶ ጆኒ፥ በሁሉም ቅርጫፎች እንዲሰራጭ በተደረገ የመስመር ታፔላ ሽያጭና ቅየራ አገልግሎትም 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል ብለዋል።

 

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

 

 

 

Advertisement