በሻንጣ ውስጥ ተጉዞ ስፔን የደረሰው ልጅ አባት ከእስር ነፃ ሆነ

                                 

የአይቮሪኮስት ዜግነት ያለው አባት የስምንት አመት ልጁ በሻንጣ ውስጥ ከሞሮኮ ተጉዞ ስፔን የደረሰ ሲሆን፤ አባትየው በቅርቡ ከእስር ነፃ ተደርጓል።

የመንግሥት ዓቃቤ ህግ አባትየውን አሊ ኡታራን ልጁን በህገወጥ መንገድ ወደ ስፔን አጓጉዟል በሚል እስር ይገባዋል ብለዋል።

ነገር ግን አባትየው ልጁ በሻንጣ ውስጥ እንደሚጓጓዝ ስለማወቁ ምንም ማስረጃ ባለማገኘቱ ቀለል ባለ ቅጣት ታልፏል።

“እኔም ይሁን አባቴ በሻንጣ እንደሚወስዱኝ አላወቅንም” በማለት አሁን የ10 ዓመቱ ልጁ አዱ ለዳኞች ተናግሯል።

ልጅየው ጨምሮ እንደተናገገረው በእስር ለአንድ ወር የቆየው አባቱ የነገረው ጉዞው በመኪና እንደሚሆን ነው።

ከሞሮኮ ወደ ስፔን ድንበር በማቋረጥ ላይ ባሉበትም ወቅት በሻንጣው ውስጥም መተንፈስ ተቸግሮ እንደነበር ይናገራል።

በአውሮፓውያኑ 2015ም በድንበር ላይ የሚገኙ ኃላፊዎች ከባድ የሆነ ሻንጣ አንዲት ሴት ስትጎትት አይተው ተጠራጥረው አስቁመዋታል።

አባትየውም 115 ዶላር የሚጠጋ የብር ቅጣትም እንዲከፍሉ ተደርጓል።

ልጅየው ከእናቱ ጋር ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር ሲሆን ለመመስከርም ወደ ስፔን አቅንቶ ነበር።

“አሁንም ሁሉ ነገር ተፈፅሟል። ከአሁን በኋላ ከሚስቴና ከልጆቼ ጋር እንዳዲስ ህይወታችንን የምናቃናበት ጊዜ ነው” በማለት ኦታራ በሰሜናዊ ስፔን አዲስ ህይወት እንደሚጀምሩም ተናግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement