በሄይቲ የኦክስፋም ቅሌት፡ተጠርጣሪዎች የአይን እማኞችን አስፈራርተዋቸዋል – Oxfam Haiti Scandal, Suspects ‘Physically Threatened’ Witnesses

                                  

ሄይቲ በሚገኘው ኦክስፋም ቅርንጫፍ በወሲብ ትንኮሳ ተከሰው የነበሩ ሶስቱ ሰራተኞች በአውሮፓውያኑ 2011 በነበረው ምርመራ የአይን እማኞችን እንዳስፈሯሯቸው ኦክስፋም አጋለጠ።

የእርዳታ ድርጅቱ ሰራተኞቹ ያደረሱትን “ብልግና” ድርጅቱ በደረሰበት የዓለም አቀፍ ግፊት ምክንያት ሪፖርቱን ለማሳተም እንደተገደደ ገልጿል።

በአውሮፓውያኑ 2011 ኦክስፋም ባወጣው ሪፖርት ስርዓት ያጓደሉ ሰራተኞች በእርዳታ ድርጅቶች እንዳይቀጠሩ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር።

ነገር ግን ይህ ማሳሰቢያ ችላ ተብሎ በወሲብ ጥቃት እንዲሁም ስርዓትን በማጓደል የተወነጀሉ ወንዶች በተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች ለመስራት እንደ ተቀጠሩ ለመረዳት ተችሏል።

በ90 አገራት ከ10ሺ በላይ ሰራተኞች ያሉት ኦክስፋም ስለሳለፉት ውሳኔዎቹ ግልፅ መሆን እንፈልጋለን በሚል በተቀባባ መልኩ ሪፖርቱን አውጥቶታል።

ይህ 11 ገፅ ያለው ሪፖርት የሰዎችን ማንነት ላለመግለፅ ስማቸው የተሰረዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የአይን እማኞች ላይ ዛቻ ያደረሱት ሶስት ወንዶች ይገኙበታል።

ዋናውን ሪፖርት ዛሬ ኦክስፋም ለሄይቲ መንግሥት የሚያቀርብ ሲሆን ለተፈፀሙ ስህተቶችም ይቅርታ እንደሚጠይቅ ተዘግቧል።

የእርዳታ ድርጅቱ ሴተኛ አዳሪነት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚላቸውን ሰራተኞቹን ምርመራ በደንብ አልተወጣም በሚል ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፍ ግፊትም እየደረሰበት ነው።

ማስፈራራና ዛቻ

በአውሮፓውያኑ 2011 ሰባት የኦክስፋም ሰራተኞች በባህርያቸው ምክንያት በሄይቲ ከሚገኘው የኦክስፋም ቅርንጫፍ እንደለቀቁ ሪፖርቱ ያሳያል።

በኦክስፋም ግቢ ውስጥ ከሴተኛ አዳሪ ጋር በመገኘታቸው አንደኛው ሲባረር ሶስቱ ከስራ እንደለቀቁ ሪፖርቱ ያሳያል። ግንኙነታቸው ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ሴቶችም ጋር ይሁን አልታወቀም።

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ በማስፈራራትና ዛቻ ምክንያት የተባረሩ ሲሆን አንደኛው ፖርኖግራፊ በመጫንና አንደኛው ደግሞ ሰራተኞችን ባለመጠበቁ ከስራቸው ተባረዋል።

ሪፖርቱም የኦክስፋም የስራ ሂደት ዳይሬክተርን ሮናልድ ቫን ሀዌርሜይረን ጠቅሶ እንደተናገረው በኦክስፋም ግቢ ውስጥ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር መገናኘታቸውን ዳይሬክተሩ በምርመራ ቡድኑ ሲጠየቁ አምነዋል።

ከምርመራ ቡድኑ ጋር ተባብረዋል በሚልም በምላሹም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተከበረ መልኩ ዳይሬክተሩ እንዲለቁ አድርገዋቸዋል።

ተቀባብቶ በወጣው ይህ ሪፖርትም የአይን እማኞች ላይ ዛቻ በማድረስ በሚልም ስማቸው አልተጠቀሰም።

ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ተወስዷል የሚለው ኦክስፋም አጠቃላይ በእርዳታው ኢንዱስትሪ ውስጥ በዚህ ጉዳይ የተዘፈቁ ሰራተኞች ወደ ሌላ አገር ሲዛወሩ ማስረጃ መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል።

“ሰራተኞች ስርዓት በማጉደል ምክንያት ከአንድ ቦታ ሲባረሩ ለሌሎች ክልሎች፣ ኤጀንሲዎች ማሳወቅና ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ያስፈልጋልም” ብለዋል።


ከፍተኛ ቦታን የተቆናጠጡ ሰራተኞች

ሪፖርቱ በስርዓት ማጉደል ምክንያት የተባረሩ ሰራተኞች ሌላ ቦታ እንዳይቀጠሩ የተሻለ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም በተቃራኒው የተባረሩ ሰራተኞች በተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች እንዲሁም በኦክስፋም ተቀጥረዋል።

ሮናልድ ቫን ሀዌርሜይረን ራሳቸው በባንግላዴሽ በሚገኝ “ሚሽን ፎር አክሽን ኤጌይንስት ሀንገር” በሚባል ድርጅት በከፍተኛ ኃላፊነት ቦታ ተቀጥረዋል።

ምንም እንኳን ድርጅቱ በሰራተኛው ላይ ምርመራ አድርጌያለሁ ቢልም ከኦክስፋም ስርዓት በማጉደል እንደተባረሩ መረጃ አልደረሰኝም ብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement