ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት ጋር በስልክ ተወያዩ – Prime Minister Hailemariam Held Talks With The German Chancellor Angela Merkel on Telephone

                                                              

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ።

የጀርመን መንግሥት ቃል አቀባይ ሽቴፈን ዛይበርትን ጠቅሶ የጀርመን ድምፅ እንደዘገበው፥ መሪዎች በትናንቱ የስልክ ውይይታቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ተወያይተዋል። 

መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የኢትዮጵያ መንግሥት በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው እስረኞች መልቀቁን አድንቀዋል።

በመንግስት እየተወሰደ ያለው እርምጃ መልካም መሆኑን ያነሱት አንጌላ ሜርክል፥ መንግሥት ይህን እርምጃውን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

መንግስት ባለፈው ጥር ወር በፌደራል ደረጃ ዶክተር መረራ ጉዲናን ጨምሮ 115 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ በማድረግ ከእስር መልቀቁ ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም ባለፈው ሳምንት እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 417 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ክስ እንዲቋረጥ ወስኗል።

በትናንትናው እለትም በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑም የሚታወስ ነው።

ከፌደራል ባለፈም ክልሎች በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተጠርጣሪና ታራሚዎችን ክስ በማቋረጥ መልቀቃቸውም ይታወቃል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement