በኢራቅ ባግዳድ ከተማ ዛሬ ጠዋት በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት የበርካቶች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ ተጠምዶ በነበረ ቦምብ በተፈፀመው ጥቃትም በትንሹ የ26 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተነገረው።
የኢራቅ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቀው፥ በቦምብ ጥቃቱ ህይወታቸውን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ 65 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ደርሷል።
በምስራቃዊ ባግዳድ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በቦብም ጥቃቱ የተጎዱት ሰዎች ቁጥር ከ90 እንደሚበልጥ ነው በመናገር ላይ የሚገኙት።
በቦምብ ጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አሁን ካለው ሊጨምር እንደሚችልም ነው የተገለፀው።
ጥቃቱን ተከትሎ እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)