የዛሬ የዕለተ ሰኞ የጥር 07 ቀን 2010 የሸገር ወሬዎች – Today Jan, 15 2018 Sheger FM Radio News

                                                           

ለባቡር መስመር ዝርጋታና የትራንስፖርት አገልግሎቱ ያስፈልጋሉ ተብለው በውጭ ሀገር ስልጠና ካገኙ ከ440 በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል ያለ ስራ የተቀመጡ አሉ ተባለ፡፡ በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በአገር ውስጥ የባቡር ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም ሊገነባ መሰናዳቱ ተነግሯል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተወሰኑ እስረኞችን ክስ ማቋረጡን ዛሬ ተናግሯል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)

ዘንድሮ እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ሊተላለፉ ይችላሉ ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ እና በፊት ገፃችሁ ላይ ጉዳት የደረሰባችሁ በነፃ ታከሙ ተብላችኋል፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ባለመቻሉ ለጊዜው በየክልላቸው መልሶ ለማቋቋም ተወስኗል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)

የ1970ዎቹንና የአሁኑ የኑሮ ሁኔታ በንፅፅር የሚያሰቃኝ “ዘመን” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሙዚየም ተከፈተ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መጪውን የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ አድርጌ ለማስመዝገብ የሚረዱትን ስራዎች ማከናወኑን ተናገረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)

በአቃቂ 9 ሰዎችን በዕቃ መጫኛ ላይ አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተገልብጦ የሰው ሕይወት አለፈ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement