የአፍሪካ ህብረት ትራምፕ የአፍሪካ አገራትን ለገለፁበት ዘረኛና ፀያፍ አነጋገር ይቅርታ እንዲጠይቁ ይፈልጋል – Donald Trump Must Apologise for “Shithole” Comments on African Countries – African Union

           

 

 

 

 

 

 

የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአህጉሪቱን አገራት ለገለፁበት ፀያፍ ንግግር በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ እያሳሰበ ነው።

ባለፈው ሀሙስ ፕሬዚዳንቱ በዋይት ሀውስ ስደተኞችን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት ላይ አገራቸው ተቀብላ የምታኖራቸው ስደተኞች በተለይም ለጥቁር ስደተኛ አገራት “እጅግ ቆሻሻ” የሚል ስያሜን የሰጠ ንግግር አድርገዋል።

በተለይም ከሄይቲ ጋር ተሳስሮ ቀረበ የተባለውን አገላለፅ ፕሬዚዳንቱ አልተናገርኩም ሲሉ አስተባብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ ንግግራቸው ላይ “ዩናይትድ ስቴትስ በተፈጥሮ አደጋ ከተጎዱ፣ በጦርነት እና በበሽታ ወረርሽኝ ውስጥ ካሉ አገራት ለሚመጡ ስደተኞች ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከምትሰጥ ኖርዌይን ከመሰሉ አገራት የሚመጡ ስደተኞችን ብትቀበል ይሻላል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ትራምፕ በንግግራቸው “ከእነዚህ ቆሻሻ አገራት ስደተኞችን ለምን እንቀበላለን” የሚልም ንግግር አውጥተዋል ነው የተባለው።

የአፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ ይህ የትራምፕ ንግግር “አስደንጋጭ እና የሚያስቆጣ” ነው ብሏል።

ህብረቱ ለዚህ ንግግራቸውም ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ይፈልጋል።

አሁን ላይ ያለው የአሜሪካ አስተዳደር አፍሪካን የተገነዘበበት መንገድ ችግር ያለበት መሆኑንም ነው የህብረቱ መግለጫ ያመለከተው።

በመሆኑም ከዚህ አስተዳደር ጋር የአፍሪካ አገራት መነጋገር አለባቸው ብሏል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement