ከዓሣና ከዶሮ ቆዳ የተለያዩ ምርቶችን ሰርቷል የተባለው የደብረ ብርሃን ቆዳ ፋብሪካ የዓሣ ቆዳ እየባከነ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
በገንዘብ እጥረት የተነሳ የአዋሽ ወንዝን ከስጋት መታደግ አልተቻለም ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
በባህል ዕቃ መሸጫ ሱቆች ውስጥ የሚሸጡ የሰዕሊያን ኮፒ ስራዎች ባለሙያው ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኝ እያደረጉ ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
የፍትህ አካላት ማሰልጠኛ ማዕከልና የፍትህ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ተዋሃዱ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ የሚያስችል የተፋሰስ ስራ ተጀመረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
ለ41 የውሃ መስመሮች አዲስ የኤሌክትሪክ ግንባታ ሊከናወን ነው፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
በኢትዮጵያ አስቸኳይ ክትባት የሚያስፈልጋቸው የእንስሳት በሽታዎች ተለይተዋል፡፡ አንድ መቶ አስራ ሰባት ሚሊዮን ክትባቶች ተሰራጭተዋል፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
የብሔራዊ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫ የሰጡት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ናቸው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
በተለያዩ ፕሮጀክቶቻቸው የተራረፉና የማይጠቀሙባቸውን ቁርጥራጭ ብረቶች በሽያጭ በማስወገድና መልሰው ለመንግስት ሀብት በማድረግ ኢትዮ ቴሌኮምና መብራት ሀይል የተሻለ አፈፃፀም አላቸው ተባለ፡፡ የስኳር ፋብሪካዎች ላይ ግን እስካሁን ችግር መኖሩን ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ