ሰሜን ኮሪያ ልዑኳን ወደ ኦሊምፒክ ልትልክ ነው – North Korea to send team to Olympic Games in Pyeongchang

                                                                 

በደቡብ ኮሪያ አስተናጋጅነት በመጪው ጥር በሚካሄደው የ2018 የክረምት ኦሊምፒክ ላይ ሰሜን ኮሪያ ልዑኳን እንደምታሳትፍ ተገለጸ።

ፓንሙንጆም በሚገኘው ፒስ ሃውስ የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ተወካዮች ለውይይት ከተገናኙ በኋላ ነው ይህ የተገለጸው።

በውድድሩ ላይ የሚላኩት ልዑካን ተወዳዳሪዎችንና ደጋፊዎችን እንደሚጨምር ተገልጿል።

የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች ለውይይት ሲቀመጡ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

“ሰሜን ኮሪያ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴ አባላት፣ አትሌቶች፣ ደጋፊዎች፣ ትርዒት አቅራቢዎች፣ ታዛቢዎች፣ የቴክዋንዶ አቅራቢዎች ቡድና እና ጋዜጠኞችን ያሳተፈ ልኡክ ለማሳተፍ አቅዳለች” ሲሉ የደቡብ ኮሪያ የውህደት ሚኒስትር ቹን ሃይ-ሱንግ መግለጻቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ውይይቱ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳደግም ያለመ ነው ስትል ደቡብ ኮሪያ ገልጻለች።

                                                                       

አጭር የምስል መግለጫሁለቱ ሃገራት ከውይይቱ በፊት ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል

የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሻክሮ ቆይቷል።

የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የተቋረጠው ፒዮንግያንግ ሮኬት በማስወንጨፏ እና የኒውክለር ሙከራ በማድረጓ ነበር።

ይህን ተከትሎም ሴዑል ጥምር የኢኮኖሚ ፕሮጀክት የሆነውን እና በሰሜን ኮሪያ የሚገኘውን የካይሶንግ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስን ፕሮጀክት አግዳለች።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement