አፕል ከልጆች የአይፎን ስልክ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ግፊቶች አይለውበታል – Financial TimesApple Faces Activist Pressure Over Children’s iPhone Use

                                                             

ፕል ኩባንያ ከታዳጊዎች እና በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች የስማርት ስልክ ሱስ ጋር ተያይዞ ላሉ ስጋቶች ምላሽ እንዲሰጥ ግፊቱ አይሎበታል።

በኩባንያው ድርሻ ያላቸው አንዳንድ ባለሀብቶች በፃፉለት ደብዳቤ የታዳጊዎች የስማርት ስልክ አጠቃቀም ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በማንሳት መፍትሄ እንዲያመጣ ይጠይቃል።

ባለድርሻዎቹ የስማርት ስልኮችን በመጠቀም የሚመጣ ያልተፈለገ የጎንዮሽ ችግር አለው ብለው እንደሚያምኑ በመግለፅ፥ ይህን ለመቅረፍ አፕል ኩባንያው በጥናት እና ምርምር መፍትሄ ይዞ እንዲመጣ ነው ያሳሰቡት።

መፍትሄውም የስልኩ መሰረታዊ ገፅታ ታዳጊዎች ለአጭር ጊዜ በስልኩ ስክሪን ላይ እንዲቆዩ የሚያደርጉ ሰው ሰራሽ ውስንነቶች ቢኖሩ ብለው ነው የመከሩት።

አፕል ታዳጊዎች ስርዓት ባለው መልኩ የሚጠቀሙትን ስልክ በማቅረብ የወላጆችን ስጋት መቅረፍ እንዳለበት ያነሱት ባለደርሻዎቹ፥ ይህ አካሄድ ገቢን በማሳደግ የባለድርሻዎቹን ጥቅም እንደሚያሳደግ አስታውቀዋል።

ኩባንያው ስልክ በመጠቀም ምክንያት በመንገድ ላይ የሚፈጠር የትራፊክ አደጋን ለመከላከል በቅርቡ በመንዳት ላይ ያሉ ሰዎች የፅሁፍ መልዕት እንዳይላላኩ የሚያግድ አንድ ስልክን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የወጣት ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ የተለያዩ እርምጃ በመውሰድ ላይ ሲሆኑ፥ በቅርቡም የማህብራዊ ትስስር ገፅ የሆነው ፌስ ቡክ ታዳጊዎች ጥብቅ የሆነ የፅሁፍ መልዕክትን ከወላጆቻቸው ጋር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ መተግበሪያ መገንባቱ እይዘነጋም።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement