በአዲስ አበባ 13 የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ለ6 ወራት አገልግሎት እንዳይሰጡ ታገዱ – 13 Motor Vehicle Inspection Centers In Addis Abeba Banned For Six Months

                                                       

በአዲስ አበባ የሚገኙ 13 የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ለ6 ወራት አገልግሎት እንዳይሰጡ መታገዳቸው ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮፖሬት ባላከው መግለጫ ተቋማቱ ለቀጣይ ስድስት ወራት አገልግሎት አይሰጡም።

ተቋማቱ በሰው ሀይል፣ በመመርመሪያ መሳሪያ አደረጃጀት፣ መረጃ አያያዝ እና ሪፖርት ላይ በተገኝባቸው ክፍተት ነው ለ6 ወራት የታገዱት።

በተጨማሪም ክትትል ከተደረገባቸው 37 ተቋማት 12 ፈቃዳቸው እንዲታደስና ጉድለታቸውን በአንድ ወር የጊዜ ገደብ እንዲያሟሉም ተደርገዋል።

አራት የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ጉድለታቸውን ካላስተካከሉ ፈቃዳቸው ሳይታደስ እንዲቆይ ይደረጋል ተብሏል።

ባለስልጣኑ ለ6 ወራት ያገዳቸውን ተቋማት ስም ዝርዝር ይፋ ከማድረግ ግን ተቆጥቧል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement