አፕል የአሮጌ አይፎን ስልኮችን ፍጥነት ለመቀነሱ ይቅርታ ጠየቀ – Apple Apologises for Slowing Older iPhones Down

                                                   

አፕል ኩባንያ የአሮጌ አይፎን ስልኮችን ፍጥነት እንዲቀንስ በማድረጉ ምክንያት በደንበኞቹ ዘነድ ለተፈጠረው ቅሬታ ይቅርታ ጠየቀ።

ከዓመታት በፊት የተመረቱ አይፎን ስልኮችን የሚጠቀሙ ደንበኞች ሰሞኑን ስልኮቻቸው ፍጥነታቸው መቀነሱን ሲገልፁ ነበር።

ደንበኞች ቅሬታ ያቀረቡት ደግሞ የስልክ የውስጥ ክፍል አገልግሎቶችን የሚያቀላጥፈውን የተሻሻለ ኢንተርናል ኦፕሬቲንግ ሲስተም (iOS) ሶፍትዌር ወደ ስልካቸው በሚጭኑበት ጊዜ ፍጥነቱ ቀንሶ ማግኘታቸውን በመጥቀስ ነው።

በሌላ በኩል ያረጀ የአይፎን ባትሪን በአዲስ መቀየር የስልኮችን ፍጥነት እንደሚጨምር መረጃው እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።

አፕል አንዳንድ ስልኮች ባትሪያቸው በማርጀቱ ምክንያት ፍጥነታቸው መቀነሱንም አምነዋል። 

በዚህም ኩባንያው እንዳለው በአውሮፓውያኑ 2018 የስማርት ስልኩ ባትሪ መዳከም ሊፈታ የሚችል ሶፍትዌር ይሰራል።

ይህም ደንበኞች የስልኮቻቸውን የባትሪ ጤንነት ለመቆጣጠር ይችላሉ ነው የተባለው።

ኩባንያው በድረ ገፁ ላይ አስፍሮታል ብሎ ቢቢሲ እንዳስነበበው ከሆነ በአይፎን 6 እና ከዛ በኋላ ባሉ ስልኮች ባትሪያቸውን ለመቀየር የሚያወጡት ዋጋ ከ79 የአሜረካ ዶላር ወደ 29 ዶላር ዝቅ ማድረጉን ገልጿል። 

ይህ ያደረገበት ዋናው ምክንያት ደንበኞቹን የሚያሳስባቸውን ነገር ለመፍታት፣ ታማኝነትን ለማትረፍ እና በአፕል ስማርት ስልክ ጥርጣሬ ላደረባቸው ሁሉ የኩባንያው እምነት ለማዳበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን በመግለፅ፥ ይህ እርምጃ ወደፊትም እንደሚገፉበት ነው የተናገረው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement