መንግስት በብሄራዊ ትንባሆ ድርጅት ከነበረው ጠቅላላ ድርሻ ውስጥ 30 በመቶውን ለውጭ ኩባንያ ሸጠ።
የሽያጭ ስምምነቱ ዛሬ በመንግስት ልማት ድርጀቶች ሚኒስቴር እና ድርሻውን በገዛው በጃፓን ትንባሆ ኢንተርናሽናል ኩባንያ መካከል ተፈርሟል።
ጃፓን ትንባሆ ኢንተርናሽናል የመንግስትን 30 በመቶ ድርሻን በ434 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው የገዛው።
ኩባንያው ከዚህ በፊት በ2008 ዓ.ም 40 በመቶውን በመቶውን የኢትዮጵያ ትንባሆ ድርጅት ድርሻን መግዛቱን ተከትሎ አጠቃላይ ድርሻውን 70 በመቶ አድርሷል።
የገዢው ኩባንያ ፕሬዚዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤዲ ፒራርድ፥ የኩባንያ ኢትዮጵያ ትንባሆ ድርጅት ያለው ድርሻ ሁለታችንም በአፍሪካ የዘርፉ ቢዝነስ ላይ ሰፊ ሚና እንዲኖረን ያስችላል ብለዋል።
“የእኛን ዓለም አቀፋዊነት እና አዲሱን አካባቢያዊ ተሞክሮ በማጣመር የኢትዮጵያ የትንባሆ ድርጅት በተሻለ ደረጃ እድገት እንዲያስመዘግብ እንደምናደርገው እተማመናለሁ ነው” ያሉት።
ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ መንግስት የትንባሆ ድርሻ ሽያጭ ግብይቱ እንዲጠናቀቅ ላደረገው አጥጋቢ ትብብር ታላቅ አክብሮታቸውን ገልፀዋል::
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)