የዛሬ የዕለተ ሐሙስ ታህሳስ 12 ቀን 2010 የሸገር ወሬዎች – Today Dec, 21 207 Sheger FM Radio News

                                                     

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ትምህርት ከቆመ 4ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)

ኢትዮጵያ በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቿን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ጥረቷን እንደቀጠለች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ተናግረዋል (የኔነህ ሲሳይ)

ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ውል በገባሁት መሰረት በአዲስ አበባ አቅም ላጡ እናቶች ነፃ የወሊድ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ግን ይህን ጉዳይ በተመለከተ የማጣራው ነገር አለ እያለ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

መገናኛ ብዙሃን እንደ ፖለቲካ ካሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ጎን ለጎን ለጤናም ትኩረት ይስጡ ተብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የግንባታ ሂደቶች ለሰራተኞች ደህንነት እምብዛም ትኩረት አይሰጡም ተብሏል፡፡ (ምስክር አወል)

በዚህ ዓመት ለእንግዳ ማረፊያዎች ደረጃ መስጠት እንደሚጀምር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement