የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና በተለያዩ ኤምባሲዎች ማስረጃ ያልቀረበባቸው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ ፈፅሟል መባሉን አስተባበለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የግል የከርሰ ምድር የእንፋሎት ሐይል የኤሌክትሪክ ማመንጪያ ለመገንባታ በትላንትናው ዕለት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
ፆታን መሰረት አድርገው የሚፈፀሙ ጥቃቶች ወደ ሕግ አካላት ቢሄዱም እንደ ሌሎች ወንጀሎች ተገቢና ተመጣጣኝ የሕግ ውሳኔ አያገኙም ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
ያለአገልግሎት ከርመው የነበሩት ለአካል ጉዳተኞች እና ለአቅመ ደካሞች ይበልጥ ያግዛሉ በሚል የተገነቡት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መወጣጫ አሳንሰሮች ሥራ ጀመሩ፡፡ (ምስክር አወል)
መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ ሸንጎ ከተባለው ቡድን ጋር ለመስራት መፈራረማቸው ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ