ለ70 ዓመታት አብረው የኖሩ ጥንዶች ለመለያየት ተገደዋል – Canada Couple Forced to Spend Christmas Apart After 70 years

                                                               

ለ70 ዓመታት አብረው በፍቅር የኖሩ ካናዳውያን ባልና ሚስት ከገና በዓል በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚለያዩ በማወቃቸው ልባቸው በሐዘን ተሰብሯል።

የ91 ዓመት ዕድሜ አዛውንት ሄርበርት ጉዲን ከ89 የእድሜ ባለፀጋ ሚስታቸው አደሬይ ጎዲን በመለየት ከአረጋውያን ረጅም ጊዜ መንከባከቢያ ተቋም ወጥተው ለህክምና ወደ ሌላ ቦታ መሄድ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል።

በዚህም በፐርዝ-አንዶቨር የሚገኘው የኒው ብሩንስዊክ የአረጋውያን ማዕከል በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ባል የአጨር ጊዜ የህክምና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እና አዛውንቶቹ ጥንዶች መለያየታቸው ግዴታ መሆኑን አሳውቋቸዋል።

ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩት ጥንዶች የመለያየት ዜና ሲሰማ በመላ ሀገሪቱ ቁጣ አስነስቷል ነው የተባለው።

የሁለቱ ጥንዶች ልጅ ዲያኔ ፊሊፕስ በፌስቡክ ማህበራዊ የትስስር ገፅ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት፥ ወላጆቼ ሲነጋገሩ እናቴ እያለቀሰች ነበር ብላለች።

የ89 ዓመቷ አዛውንት አደሬይ ጎዲን የዘንድሮው የገና በዓል ሁለታችን ተለያይተን የምናከብረው በመሆኑ አስከፊው ገና ነው ብለዋል።

እንዲዚህ ዓይነቱ የገና በዓል የመጨረሻው እንደሚሆን አስባለሁ፤ የማዕከሉ ሰዎች ግን ለምን ገናን አብረን አክብረን እስክንጨርስ መጠበቅ አልቻሉም?” በሚል የሀዘን ስሜት ተናግረዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement