የዛሬ የዕለተ ሰኞ የታህሳስ 9 ቀን 2010 ዓ.ም የሸገር ወሬዎች

                                           

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱን እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የሰው ሞትና የአካል ጉዳት ያደረሱ ግጭቶችም በአስቸኳይ መፍትሄ ማግኘት ካልቻሉ እንደሀገር አሳሳቢ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ (አስፋው ስለሺ)

የኢጋድ አባል አገሮች ጉባዔ በሚንስትሮች ደረጃ ትላንትና ተጀምሯል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በ2.46 ቢሊየን ብር ከቃሊቲ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ የመንገድ ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (አንተነህ ሀብቴ)

በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች ወርቅ ቢመረትም ከወርቅ ወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ግም አሳሳቢ በሆነ መልኩ እያሽቆለቆለ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን )

በአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ እገዛ በብሪቲሽ ካውንስል አስተባባሪነት በ3 የአፍሪካ ቀንድ ሐገራት ላይ ሊሰራ የነበረው የሆላ ፕሮጀክት ወደ መጨረሻ ምእራፍ መቃረቡ ተነገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)

ባለፉት 5 ዓመታት የቁልቁለት መንገዱን የተያያዘው የማዕድኑ ዘርፍ ዘንድሮም ቀና ብሎ መራመድ የሚችል አይመስልም ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement