የጆሮ ማዳመጫ ይዋዋሳሉ?

                                          

እንግዲያዉስ የጆሮ ማዳመጫ በመዋዋስ መጠቀም የሚያደርሰዉን ጉዳት ለግንዛቤ እነሆ::

1. የጆሮ ማዳመጫ የምንዋዋስ ከሆነ ቫይረስ በማዳመጫዉ በኩል ስለሚተላለፍ በጆሮአችን ዉስጥ እንፌክሽን ይፈጠራል፡፡

2. በሂደት የመስማት ችሎታን ይቀንሳል፤ከፍተኛ የመስማት ችግርም ያስከትላል፡፡

3.የጆሮ ማዳመጫ ቀዳዳዉ ጠባብ ስለሆነ አየር እንደ ልብ ባለመዘዋወሩ የጆሮ እንፌክሽን በከፍተኛ ደረጃ ይፈጠራል፡፡

4. ጆሮአችን ዉስጥ በተወሰነ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ የህመም ስሜት ያመጣል፡፡

5. በጆሮ ማዳመጫ የሚፈጠሩ ኤሌክትሮ ማግኔት ሞገድ አዕምሯችንን በከፍተኛ ይጎደዋል፡፡
6. ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ለሕይወት አስጊ የሆኑ አደጋዎች እንደ መኪና አደጋ ሲፈጠር የሚጎዱ የጆሮ ማዳመጫ ያደረጉ ሰዎች ናቸዉ(፡ይህም በአከባቢያቸዉ ያለዉን ስለማይገነዘቡ)፡፡

7. ዉስጠኛዉ የጆሮአቺን ክፍል ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ስለሆነ የጆሮ ህመምና ብሎም የመስማት መሳን አደጋ ያስከትላል፡፡

መፍትሔ

1.በመዳመጫ መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ጠባቡን ሳይሆን ሰፋ ያዉን ማዳመጫ መጠቀም፡፡

2.የጆሮ ማዳመጫ አለመዋዋስ

3.የጆሮ ማዳመጫ ክዳን ስፖንጅ አይነቱን በወር አንድ ጊዜ መቀየር፤ስፖንጅ የለሌዉን ደግሞ ንጽናዉን መጠበቅ፡፡

4. በሚጓዙበት ጊዜ የጆሮ ማዳመጫ አለመጠቀም፡፡

5.የሙዚቃ ድምጽ ቀንሶ ማዳመጥ፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ

Advertisement