NEWS: በናይጀሪያ በደረሰ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት በትንሹ 50 ሰዎች ተገደሉ – Nigeria Suicide Bombing Kills 50 in Adamawa State

                                                                               

በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጀሪያ በደረሰ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት በትንሹ 50 ሰዎች ተገደሉ።

የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት የተፈፀመው፥በአዳማዋ ግዛት በሚገኝ መስጅድ ላይ መሆኑን የናይጀሪያ ፖሊስ አስታወቋል።

እድሜው 17 ዓመት የሚጠጋ ታዳጊ በግዛቱ ሙቢ በተባለች ከተማ በሚገኝ መስጅድ በሰውነቱ ያጠመደውን ቦምብ ሰዎች ለጧት አምልኮ በተሰባሰቡበት ወቅት በማፈንዳት ጥቃት አድርሷል።

በዚህም አጥፍቶ ጠፊው ታዳጊ እና ከ30 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።

የአዳማዋ ግዛት ፖሊስ ቃል አቀባይ አቡበከር ኦትማን ከፍተኛ ጉዳይ የደረሰባቸው ሰዎች ስላሉ ሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ጠቁመዋል።

አጥፍቶ ጠፊው የአምልኮ ስርዓት የሚፈፅም መስሎ ወደ መስጅዱ በመግባት ጥቃቱን ማድረሱ ነው የተገለጸው።

ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ ቡድን ባይኖርም፥ በናይጀሪያ የሽብር ተግባር እያደረሰ የሚገኘው ቦኮሃራም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ከዚህ ቀደም ማድረሱ ይታወቃል።

የሽብር ቡድኑ በሀገሪቱ ጥቃት ማድረስ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በትንሹ 20 ሺህ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ከ2 ሚሊየን ያላነሱ ዜጎች ደግም ከመኖሪያ ቀየታቸው ተፈናቅለዋል።

ሙቢ ከተማ በፈረንጆቹ 2014 ቦኮሃራም እንድትቆጣጠራት ቢታወቅም፥ የናይጀሪያ ጦር በ2015 የሽብር ቡድኑን ከተማዋን እንዲለቅ አድርጎታል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement