ማይክሮሶፍት ያለ እጅ ንክኪ አእምሮን በማንበብ ብቻ የሚሰሩ ኮምፒውተሮችን ለመስራት አቅዷል – Microsoft Plans The Future Of “Mind-Reading Computers”

                                                                        

ግዙፉ የተክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ያለ እጅ ንክኪ የሰዎችን አእምሮ በማንበብ ብቻ የሚሰሩ ኮምፒውተሮችን ለመስራት ማቀዱ ተሰምቷል።

ኩባንያው ለኮምፒውተሩ የፈጠራ ባለቤትነት መብትን የጠየቀ ሲሆን፥ የባለቤትነት መብቱም የሰውን አእምሮ ብቻ በማንበብ የሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ የሚያተኩር ነው ተብሏል።

ለምሳሌም ሰዎች ያለ እጅ ንክኪ ከኤሌክትሮኒክስ መገልገያቸው ላይ ሙዚቃ እንዲክፍቱ እና እንዲቀይሩ፤ ድምጹን እንዲጨምሩ እና እንዲቀንሱ እንዲሁም የመሳሰሉት ይገኝበታል።

እንዲሁም ኮምፒውተሩን ባስፈለገን ጊዜ በእጅ ንክኪ እንዲሰራ አሊያም ያለ እጃችን በአእምሯችን ብቻ በማዘዝ እንዲሰራ በማድረግ መቀያየር እንደሚቻለም ተነግሯል።

በእቅድ ደረጃ ያለው ቴክኖሎጂው ወደ ፊት በኮምፒውተር ላይ ለመፃፍ የሚያገለግለውን ኪቦርድን ጨምሮ እንደ ማውዝ ያሉ ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያስቀር ነው።

በምትኩ ተጠቃሚዎች አእምራችውን የሚያነብ የቴክኖሎጂ ቁስ መልበስ ሊጠበቅባቸው ይችላልም ተብሏል።

ኮምፒውተሩ አእምሮን ከማንበብ በተጨማሪም የሰዎችን የእጅ እንቅስቃሴን እና አካላዊ ምልክቶችን በመከታተል ሊሰራ እንደሚችልም ተጠቅሷል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement