ከስልጣን የተባረሩት የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ሃገር ጥለው ተሰደዱ – Zimbabwe’s Vice-President Emmerson Mnangagwa Who had Been Removed From his Post Left The Country

                                                             

ባሳለፍነው ሰኞ ከሥልጣን የተባረሩት የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለሕይወታቸው ሰግተው ከሃገር መሸሻቸውን አጋሮቻቸው ተናገሩ።

የ93 ዓመቱ ፕሬዝደንት ሙጋቤ የቀድሞ ምክትላቸው ሥልጣኔን ለመውሰድ ሲያሴሩ ነበር ብለዋል።

ረቡዕ ዕለት ሙጋቤ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ”ምናንጋግዋ ወደ ቤተክርሰቲያን ሄዶ እኔ መቼ እንደምሞት ነብዩን ጠየቀ ንብዩም እኔ ሳልሆን እሱ ቀድሞ እንደሚሞት ነገርውታል” ብለዋል።

የሙጋቤ በባለቤት ቀዳማዊ እመቤት ግሬስ ሙጋቤ ምናንጋግዋን ሊተኩ እንደሚችሉ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

”እባቡ በሃይል ጭንቅላቱን መመታት አለበት” በማለት ከዚህ በፊት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው እንዲያነሱ ሮበርት ሙጋቤን ሲወተውቱ እንደነበርም ተወስቷል።

በቀጣይ ወር ገዥው ‘ዛኑ’ ፓርቲ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ይሾማሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ትናንት ዛኑ ፓርቲ የቀድሞ የደህንነት ሹሙንና ምክትል ርዕሰ-ብሔር ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከፓርቲ አባልነት ሰርዟል።

”ምናንጋግዋን ለረዥም ጊዜ ድብቅ ማንነቱን እናውቅ ነበር። ለኔ ቅርብ በመሆኑ ብቻ በጀርባዬ አዝዬው ወደ ፕሬዝደንት ወንበር የምወስደው መስሎት ነበር። እኔ ግን አልሞትኩም፤ ከስልጣንም አልወረድኩም” ሲሉ ሙጋቤ በሃራሬ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

                                                                  

ሃገር ጥለው የተሰደዱት የቀድሞ ፕሬዝዳንት “ወደ ሃገሬ ተመልሼ ሙጋቤን እና ባለቤታቸውን ፓርቲውን በመቆጣጠራቸው እና ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ለፍርድ አቀርባቸዋለሁ” ብለዋል።

ጨምረውም የዛኑ ፓርቲ ባለስልጣናትን ፓርቲው እንዲጠለፍ እና ”የግል ንብረት” እንዲሆን ተባብረዋል በማለት ኮንነዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement